
“ምርጫው በሁሉም አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ ነው” ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው ጠቅላላ ምርጫ በሁሉም አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ።
የቦርዱ ሰብሳቢ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ምርጫ በሚካሄድባቸው ሁሉም አካባቢዎች የድምፅ አሰጣጡ በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ ነው።
በአብዛኞቹ ምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ ጀምረው ምርጫውን እያከናወኑ መሆኑንም ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ ዘጠኝ ምርጫ ጣቢያዎች “ሃላፊነት የጎደላቸው” ምርጫ አስፈፃሚዎች በቦታው ሳይገኙ መቅረታቸውን ጠቅሰዋል።
ሆኖም ሌሎች 27 አስፈፃሚዎችን ቃለ መሃላ በማስፈፀም ስራ እንድጀምሩ በመደረጉ የምርጫ ሂደቱ ዘግይቶ ተጀምሯል ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል አምቦ አንድ የምርጫ ጣቢያ ምንም ሳይፈጠር የተደናገጡ ምርጫ አስፈፃሚዎች ቦታውን ለቀው ቢሸሹም የተፈጠረ ችግር ባለመኖሩ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎችና እጩዎችን ተሳትፎና ተዘዋውሮ የመታዘብ መብት መገደብ የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑንም ሰብሳቢዋ ተናግረዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ