ለሀገር ልማትና አንድነት ይጠቅማል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን በነጻነት መስጠታቸውን በቻግኒ ምርጫ ክልል የስጋዲ ምርጫ ጣቢያ ላይ ድምጽ የሰጡ አርሶ አደሮች ተናገሩ።

74
ለሀገር ልማትና አንድነት ይጠቅማል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን በነጻነት መስጠታቸውን በቻግኒ ምርጫ ክልል የስጋዲ ምርጫ ጣቢያ ላይ ድምጽ የሰጡ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በቻግኒ ምርጫ ክልል ከተቋቋሙት 72 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል 53ቱ በጓንጓ ወረዳ ስር ያሉ ናቸው።
በወረዳው ስጋዲ ቀበሌ የስጋዲ ምርጫ ጣቢያ ያነጋገርናቸው አርሶ አደር ዘውዲቱ አባዤ ወቅቱ የእርሻ ተግባራት የሚከናወኑበት ቢሆንም ለሕዝብ ጥቅም የሚቆመውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ በማለዳው የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው በነጻነት ድምጻቸውን መስጠታቸውን ገልጸዋል።
አርሶ አደር ንጉሤ በቀለ በበኩላቸው “በአሁኑ ወቅት የዘራሁትን የምኮተኩትበት፤ ያለሰለስኩትን መሬት የምንዘራበት ቢሆንም ከሀገር አይበልጥም በማለት ሥራየን አቁሜ ወኪሌንን መርጫለሁ” ነው ያሉት።
በቀጣይም የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እንዲያድግ ከሚመረጠው መንግሥትና ሰፊ ሥራ ይጠይቃል ብለዋል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ነገ በየምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ይደረጋል።
ዘጋቢ:- ስማቸው እሸቴ – ከቻግኒ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ የመሞከሩ አካላት ሕጋዊ ርምጃ ተወሰደባቸው።
Next article“ምርጫው በሁሉም አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ ነው” ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡