በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ የመሞከሩ አካላት ሕጋዊ ርምጃ ተወሰደባቸው።

154
በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ የመሞከሩ አካላት ሕጋዊ ርምጃ ተወሰደባቸው።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ።
የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ጋልሜቻ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ግለሰቦቹ የተቀጡት ሰላማዊውን የምርጫ ሂደት ለማወክ በመሞከርና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ስንታየሁ ዑርግዬ የተባለ ግለሰብ በአዳማ ከተማ አባገዳ ክፍለ ከተማ ኦዳ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘቱ በአዋጅ ቁጥር 1177/2011 ዓ.ም የተቀመጠን ክለከላ በመጣስ ወንጀል ተከሶ መቀጣቱን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በዚሁ ክፍለ ከተማ በምርጫ ጣቢያ ስድስት ከጠዋቱ 2:40 ላይ ከማል አብዶ የሚባል ግለሰብ ድምፅ ሰጪ መስሎ ድምፅ መስጫ ጣቢያው ድረስ በመግባት ሂደቱን ለማወክ ጥረት በማድረጉ መቀጣቱን አመልክተዋል።
በምርጫ ወቅት ሊኖሩ የሚችሉ ወንጀሎችን ለመመልከት የተቋቋመው የአዳማ ወረዳ የወቅታዊ ጉዳይ ችሎት ግለሰቦቹ በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቀዋል።
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ የተገኘው ስንታየሁ ዑርግዬ በአንድ ዓመት እስራትና በ5 ሺህ ብር መቀጣቱን ተናግረዋል።
ምርጫውን ለማስተጓጎል የሞከረው ከማል አብዶ የተባለ ግለሰብ ደግሞ በስምንት ወር እስራት መቀጣቱን ኢንስፔክተር ወርቅነሽ አስታውቀዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ሰላማዊ ሆኖ መጥቶ ሕዝቡ በሰላም ወደ ቤቱ ሲመለስ ደስ ይለናል” ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ካሳ ፣ “የምትጠባ ህጻን ከቤት ትቸ ነው ውጭ ያደርኩት” ዋና ኢንስፔክተር ሻሼ
Next articleለሀገር ልማትና አንድነት ይጠቅማል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን በነጻነት መስጠታቸውን በቻግኒ ምርጫ ክልል የስጋዲ ምርጫ ጣቢያ ላይ ድምጽ የሰጡ አርሶ አደሮች ተናገሩ።