
‹‹ምርጫዉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል›› የእነዋሪ ከተማ ምርጫ ክልል መራጮች
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በእነዋሪ የምርጫ ክልል በሚገኙ 63 የምርጫ ጣቢያዎች ነዉ የእነዋሪ ከተማ ነዋሪዎች ድምጻቸዉን እየሰጡ የሚገኙት። በእነዋሪ የምርጫ ክልል እንኮራ 1ሀ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተዉ ድምጻቸዉን የሰጡት አቶ አስናቀ በነበሩ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ተናግረዋል።
“ምርጫዉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታችንን መወጣት የሁላችንም ድርሻ ነዉ” ብለዋል።
በእንኮራ 1ለ የምርጫ ጣቢያ ድምጽ የሰጡት አቶ በላይ መኮንን በበኩላቸዉ ዜጎች ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ የአካባቢያቸዉን ሰላም መጠበቅ ላይ ሊሠሩ እንደሚገባ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል።
የእነዋሪ የምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ኀይሉ ደጀኔ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ለአሚኮ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡- ሀብታሙ ዳኛቸዉ – ከእነዋሪ ከተማ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ