
ባሕር ዳር፡ መስከረም 9/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአውሮፓውያኑ 2019 ኢትዮጵያ ትልቁን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በማስተናገድ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት በቀዳሚነት መቀመጧ ነው የተገለጸው፡፡
እንግሊዙ ኩባንያ ‹ኧርነስት እና ያንግ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ማማከር አገልግሎት› ባሰራጨው መረጃ እንዳለው በምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ 7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ቀጥታ መዋዕለ ንዋይ ስባለች፡፡
ኬንያ 2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ስትስብ ታንዛኒያ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በመሳብ ይከተላሉ፡፡
ምንጭ፡- አፍሪካ ኒውስ
በኪሩቤል ተሾመ