
‹‹ችግኝ እየተከልን ዴሞክራሲንም እንተክላለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር)
ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የምርጫ ድምጽ ለመስጠት በአጋሮ-በሻሻ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በብዙ መልኩ የሚያስደምም ነው ብለዋል፡፡
ለምርጫው ከ2 ሺህ 70 በላይ የሚዲያ ሙያተኞች በመቶ በሚጠጉ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰማርተው ቀጥታ እያስተላለፉ ነው፣ ይሄ በኢትዮጵያ ታሪክ ሆኖ አያውቅም ነው ያሉት፡፡ አሁን ላይ በሰለጠነው ዓለም እንዳለው በቀጥታ እየተላለፈ ሕዝቡ ምርጫውን ራሱ እያዬ የሚያስፈጽምበት መንገድ የሚያኮራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የደኅንነት ተቋማት ከአንድ ጣቢያ ምርጫውን በብዙ መንገድ እየተከታተሉ ነውም ብለዋል፡፡ ምርጫው ከእስካሁኑ በብዙ መንገድ የተሻለ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢያሸንፉም ባያሸንፉም ቢመረጡም ባይመረጡም፣ ከውጭ ያለውን ጫና አንሰማውም ብለው በመሳተፋቸው ክብር ይገባቸዋል ነው ያሉት፡፡
ምርጫው በኢትዮጵያ የዴሞክራሲን ድባብ እያሳዬ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
“ችግኝ እየተከልን ዴሞክራሲንም እንተክላለን” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ