
በምርጫ ሂደቱ ሕገ ወጥ ተግባራት የሚፈጽሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም 6ኛው ሀገራዊ እና ከልላዊ ምርጫ ዛሬ ከንጋቱ 12፡00 ጀምሮ በሀገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጅ በአንድ አንድ ቦታዎች ሕገወጥ ተግባራት መኖራቸውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል፡፡
ወይዘሪት ብርቱካን በአማራ እና በደቡብ ክልል የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የእጩ ተወዳዳሪ ወኪሎቻቸውን ማንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ሪፖርት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
የታችኛው የአስተዳድር መዋቅር ችግሩን መፍታት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ችግሩን ለመፍታት እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል፡፡ በምርጫው ሂደት ሕገ ወጥ ተግባራትን የሚፈጽሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም አሳስበዋል፡፡
በትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ