
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሂር ሙሐመድ የምርጫ ካርድ ባወጡበት በጎንደር ዙሪያ ምርጫ ክልል 4 በእንፍራንዝ ከተማ ቀጠና 5 ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሂር ሙሐመድ የምርጫውን ሀገራዊ እንቅስቃሴም እየተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሚወዳደሩበት የምርጫ ክልል የተለየ ችግር አላየሁም ብለዋል፡፡
ምርጫ ፉክክር በመኾኑ ውጤቱን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ክፍተቶች ካሉም በሕጋዊ መንግድ እንዲታዩ እንደሚያደርጉ ነው ለአሚኮ የገለጹት፡፡
ዘጋቢ፡-ደጀኔ በቀለ – ከእንፍራንዝ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ