
በደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ነዋሪዎች ድምጽ እየሰጡ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ በደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ መራጮች በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ከጥዋቱ 12፡00 ጀምረው ድምጽ በመስጠት ላይ ናቸው። የወረዳው ነዋሪ አርሶ አደር አበባው አሰፋ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
ምርጫውን በሰላም እየተካሄደ እንደኾነ እና የአስፈጻሚዎቹ መስተንግዶ መልካም መሆኑን አርሶአደሩ ለአሚኮ ተናግረዋል።
የወረዳው ነዋሪ ወይዘሮ ስመኝ ታደሰ “ያለ አንዳች ጫና መርጫለሁ፤ ሀገራችን ሰላም ትሁን፤ ሁሉም ሰው ለሰላም ዘብ ይቁም” ብለዋል።
በቦረና ወረዳ ደብረሲና ቁጥር 1 ምርጫ ክልል 74 ሺህ 336 መራጮች ተመዝግበዋል። 100 የምርጫ ጣቢያዎች በምርጫ ክልሉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡- ጀማል ይማም-ከቦረና
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ