
ምርጫውን በሰላም አጠናቅቆ ውጤቱን ለመቀበል መዘጋጀት እንደሚገባ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ ድምፅ የሰጡት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር በምርጫው ሒደትና የምርጫ ቦርድን ውጤት ከመቀበል አንጻር አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ምርጫውን በሰላም አጠናቅቆ ውጤቱን ለመቀበል መዘጋጀት እንደሚገባም ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች በምርጫው መሳተፋቸውንና ውጤቱ በጉጉት የሚጠበቅ መኾኑንም አቶ አገኘሁ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ