
በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራንዮ ምርጫ ክልል መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኮልፌ ቀራንዮ ምርጫ ክልል 24 ወረዳ ዘጠኝ ምርጫ ጣቢያ አንድ እና ሁለት መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነዉ፡፡ ክፍለ ከተማዉ 2መቶ 28 ምርጫ ጣቢያ እና ሁለት ምርጫ ክልሎች አሉት። በክፍለ ከተማዉ ከ260 ሺህ ሰዉ በላይ ለመራጭነት ተመዝግቧል፡፡ አሚኮ ያነጋገራቸዉ መራጮችም ምርጫ የነገን እድል መወሰኛ በመሆኑ ካርድ ያወጣ ነዋሪ በመምረጥ የነገ መብቱን ዛሬ በካርድ ማስከበር እንዳለበት አስታዉሰዋል፡፡
በተለይም መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲመጡ የመራጭነት ካርድ፣ ማንነትን የሚገልጽ ሰነድ/መታወቂያ በመያዝና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማደረግ እንዳለባቸው አስታዉሰዋል።
በአዲስ አበባ በአጠቃላይ 1ሺህ 848 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ።
ለነገ ትዉልድ አሻራን በማሳረፍ ሀገር ወዳድነትን ማሳየት ይገባል ያለዉ የክፍለ ከተማዉ ነዋሪ አቶ እስማኤል ጀቢር ከምርጫዉ ጎን ለጎን ችግኝ በመትከል ሁሉም ሀገር ወዳድነቱን ሊያሳይ ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጺዮን አበበ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ