በስማዳ ምርጫ ክልል አንድ ከጠዋቱ 12 ስዓት ጀምሮ ድምጽ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

104
በስማዳ ምርጫ ክልል አንድ ከጠዋቱ 12 ስዓት ጀምሮ ድምጽ መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ረጃጅም ሰልፎች ገና በንጋቱ በበርካታ ጣቢያዎች ተስተውሏል፡፡ አቅመ ደካሞች ይደገፋሉ፤ አካል ጉዳተኞችም ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡
ይበልጣል መለሰ አይነስውር ወጣት ነው፡፡ ገና በጠዋቱ ነው ድምፅ ለመስጠት ምርጫ ጣቢያ የተገኘው፡፡ ሰልፍ አላስጠበቁኝም፣ ድጋፋቸውም አልተለየኝም ብሏል፡፡ የሚበጀንን ልመርጥ የምፈልገውን ሰው ድጋፍ እንዲያደርግልኝ ይዤ መጥቻለሁ ነው ያለው፡፡
64 የምርጫ ጣቢያዎችን አቅፎ 35 ሺህ 833 መራጮች የተመዘገቡበት የስማዳ ምርጫ ክልል 1 ከጠዋቱ 12፡00 ስዓት ጀምሮ መራጮች ድምፅ መስጠት ጀምረዋል፡፡
በወገዳ ከተማ ውስጥ በሚገኙ አምስት የምርጫ ጣቢያዎች ተንቀሳቅሰን እንዳየነው መራጮች ከማለዳው 11፡00 ስዓት ጀምረው ተራ ይዘው ሲጠባበቁ አስተውለናል፡፡
መራጮችም ድምጽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው – ከስማዳ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራንዮ ምርጫ ክልል መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነው፡፡
Next article‹‹ምርጫው የኢትዮጵያን ሰርግ፣ የልጅህን ሰርግ የምታዬበት የሚመስል ድባብ ነው ያለው›› ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክበረት