የአለፋ-ጣቁሳ ነዋሪዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው፡፡

200
የአለፋ-ጣቁሳ ነዋሪዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አለፋ ወረዳ ሻሁራ ምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ሲሰጡ ያገኘናቸው ሼህ እስማኤል ይመር እንደገለጹት ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄዱ ሀገራዊ ምርጫዎች ድምጻቸውን ሲሰጡ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ዛሬ በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫም ይወክለኛል የሚሉትን ፓርቲ የምርጫ ካርዳቸውን ተጠቅመው መብቴን ያስጠብቅልኛል፣ ሀገሬን ያሳድግልኛል ብየ ያሰብኩትን መርጫለሁ ነው ያሉት፡፡
ሼህ እስማኤል ይመር እንደነገሩን ከሆነ ምንም እንኳን ማንም ሳይቀድማቸው ድምጽ ለመስጠት ከ11:30 በፊት በምርጫ ጣቢያው የተገኙ ቢሆንም ከእሳቸው በፊት በርካታ ድምጽ ሰጭዎች ቀድመዋቸው እንዳገኟቸው ነው የነገሩን።
ድምጻቸውን ያለማንም ገደብ በነፃነት መስጠታቸውን ያስታወቁት ሼህ እስማኤል ምርጫ ያወጡ ሌሎች ዜጎች ድምጻቸው ዋጋ ያለው መሆኑን አውቀው ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመምጣት ድምጻቸውን እንዲሰጡም መክረዋል።
በአለፋ-ጣቁሳ ሁለት ምርጫ ክልል 68 ሺህ 4 መቶ 37 ሰዎች ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ ወስደዋል።
በምርጫ ክልሉ መራጮች ድምፅ ለመስጠት የሚችሉባቸው 98 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን አሚኮ ቅኝት ባደረገባቸው በሻውራና አካባቢው የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምጽ መስጠት ከሚችሉበት ሰዓት ጀምሮ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
በምርጫ ክልሉ በአጠቃላይ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች ይወዳደራሉ። ለክልል ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪዎቻቸውን ነው ያቀረቡት።
ዘጋቢ፡- ሀይሉ ማሞ – ሻሁራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበከሚሴ ከተማ መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው፡፡
Next articleበአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራንዮ ምርጫ ክልል መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነው፡፡