በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የምርጫ ክልል መራጮች ድምፅ እየሰጡ ነው፡

148
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የምርጫ ክልል መራጮች ድምፅ እየሰጡ ነው፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ 6ኛዉን ጠቅላላ ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ እያካሔደች ነው። በማእከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ በምርጫ ክልል አራት ሥር ከተካተቱት መካከል በእንፍራንዝ ከተማ አንዱ የምርጫ ጣቢያ አሚኮ ተገኝቷል።
በምርጫ ጣቢያዉ ድምፅ ከመሰጠቱ አስቀድሞ ታዛቢዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና የሲቪክ ማኅበራት በተገኙበት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች፣ የድምፅ መስጫ ሳጥን ባዶ መኾኑ ከተረጋገጠ እና የሚስጥር ቁልፍ ከተሰጠው በኋላ በቃለ ጉባኤ ተፈራርመዋል፡፡
ድምፅ መስጠት ከመጀመሩ አስቀድሞ በጣቢያዉ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና ታዛቢዎች ምርጫ መጀመር እንደሚቻል ቃለ ጉባኤ ተፈራርመዋል። በተመዘገቡት መራጮች ልክ የድምፅ መስጫ ወረቀት መዘጋጀቱንም መረዳት ተችሏል።
አሚኮ እንደታዘበው በምርጫ ጣቢያዉ ለኮሮናቫይረስ መከላከል አስፈላጊዉ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው፡፡ መራጮችም ከ12:00 ቀደም ብሎ በድምፅ መስጫ ጣቢያዉ ተገኝተዋል። የድምፅ መስጫ ሰዓቱ እንደደረሰም ድምፅ መስጠት ተጀምሯል።
በምርጫ ክልሉ ሥር 41 ምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲኾን 27 ሺህ 935 ሰዎች የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ከምርጫ ክልሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
አሚኮ በተገኘበት ምርጫ ጣቢያ ደግሞ 735 የከተማዋ ነዋሪዎች የመራጭነት ካርድ ወስደዋል።
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ – ከእንፍራንዝ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ ማጠብያ ምርጫ ክልል ደለጉ ሀ እና ለ የምርጫ ጣብያዎች መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነው።
Next articleበከሚሴ ከተማ መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው፡፡