
በምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ ማጠብያ ምርጫ ክልል ደለጉ ሀ እና ለ የምርጫ ጣብያዎች መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በገለጉ ለ የምርጫ ጣብያ ሲመርጡ ያገኘናቸው መራጮች የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ ከ11:00 ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣብያው መሄዳቸውን ገልጸዋል። በሰላም የሚፈልጉትን እጩ መምረጣቸውንም ነግረውናል።
ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም ቀድመው መርጠው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ መክረዋል። ምርጫው ከመጀመሩ በፊት የተፎካካሪ ፓርቲ ታዛቢዎች እና የምርጫ አስፈጻሚዎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን እና የድምጽ መስጫ ሳጥኖችን በማረጋገጥ መራጮች ድምጽ መስጠት እንዲጀምሩ ተደርጓል።
በቋራ ማጠቢያ የምርጫ ክልል በሚገኙ 63 የምርጫ ጣብያዎች 10 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ- ከቋራ ማጠብያ ምርጫ ክልል
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ