
“የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መገለጫዉ ውጤቱን በሰላም መቀበል ነው” ዶክተር ድረስ ሳኅሉ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ (ዶክተር) የምርጫ ካርድ ባወጡበት የዳግማዊ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ፍኖተ ቀበሌ ‘ፍኖተ 2መ-1’ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል፡፡
የዳግማዊ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ፍኖተ ቀበሌ ፍኖተ 2መ-1 የምርጫ ጣቢያ 6ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት መራጩ ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ ነበር የተገኘው፡፡ በምርጫ ጣቢያዉ ሰልፍ ይዘው ድምፃቸዉን የሰጡት ዶክተር ድረስ ሳኅሉ የምርጫ ጣቢያዉን መስተንግዶና ምቹነት አድንቀዋል፡፡
ዶክተር ድረስ የምርጫ ካርድ ያወጣ ዜጋ ሁሉ ዛሬ የምርጫ ካርዱን ባወጣበት የምርጫ ጣቢያ ተገኝቶ የመምረጥ ሀገራዊ ኀላፊነቱን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ “የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መገለጫዉ ውጤቱን በሰላም መቀበል ነው” ያሉት ዶክተር ድረስ ውጤቱን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ መጠበቅ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
እርሳቸውም እንደተወዳዳሪ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚገለፀውን ውጤት በሰላም ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- የማነብርሃን ጌታቸው – ከባሕር ዳር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ