በቃሉ 1 የምርጫ ክልል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ መስጠት ተጀምሯል።

107
በቃሉ 1 የምርጫ ክልል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ መስጠት ተጀምሯል።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በምርጫ ክልሉ ከሚገኙ አሚኮ ቅኝት ባደረገባቸው የምርጫ ክልሎች ኅብረተሰቡ ለምርጫ ሂደቱ ከማለዳ 12 ሰዓት በፊት ሰልፍ ይዞ ሲጠባበቅ ተመልክተናል። በአንድ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ተገኝተንም የምርጫ ሂደቱን አጀማመር ቃኝተናል። የምርጫው ሂደትም 12:02 ላይ ተጀምሯል።
መራጮች ድምፅ ከመስጠታቸው በፊት ታዛቢዎች እና የፓርቲ ተወካዮች ባሉበት የምርጫ ቁሳቁስ የያዘ ሰማያዊ ሳጥን ተከፍቷል። የድምፅ መስጫ ሳጥኖችም ባዶ መሆናቸው ተረጋግጧል። በምርጫ ጣቢያው ኃላፊም ስለ ምርጫ ቁሳቁስ አጠቃቀምና የምርጫ ሂደት ገለፃ ተደርጎ እና የስምምነት ቃለ ጉባኤ ተይዟል።
የመምረጡ ተግባርም ከምርጫ አስፈጻሚዎችና ታዛቢዎች ነው የጀመረው።
ለመራጮችም የምርጫው ሂደት ገለፃ እየተደረገላቸው ይገኛል፤ መምረጥም ጀምረዋል።
በቃሉ 1 የምርጫ ሂደት 85 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡- ጀማል ሰይድ – ከኮምቦልቻ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ 8 የምርጫ ክልሎች 805 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ። ከ ስምንቱ የምርጫ ክልሎች አንዱ በሆነው ግራርጃርሶ የምርጫ ክልል 64 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ።
Next article“የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መገለጫዉ ውጤቱን በሰላም መቀበል ነው” ዶክተር ድረስ ሳኅሉ