የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከግብዓት ማሟላት ጀምሮ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት አስታወቀ።

81
የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከግብዓት ማሟላት ጀምሮ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 04/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስቴር ከኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት ጋር በመተባበር ከክልል እና ከተማ አሰተዳደሮች ጋር በሀገር አቀፍ የኮሮናቫይረስ ሥርጭት ጥናት ውጤት ዙሪያ ዉይይት እያደረገ ነው። በመርኃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት ምክትል ዳይሬክተር አስቻለዉ ዓባይነህ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ልዩ ልዩ ተግባራት ቢከናወኑም ከቫይረሱ ሥርጭት መጨመር ጋር ተያይዞ የግብዓት እጥረቶች ማጋጠማቸዉን ገልጸዋል።
እስካሁን ድረስ የኮሮናቫይረስን በመመርመር ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ ደረጃ ላይ ትገኛለች ሲሉም ጠቅሰዋል። የመመርመሪያ ኪት አቅርቦት ችግርንም ለመፍታት በሀገር ዉስጥ እንዲመረት የማድረግ ሥራዎች ተሠርተዋልም ብለዋል። ተቋማት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አጠቃቀም ላይ ችግሮች እንደታዩባቸዉም ተነስቷል። ዳሬክተሩ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እና ሌሎች የህክምና ግብዓቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ ተደርጓል ብለዋል።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዲኤታ ሙሉ ነጋ (ዶ.ር) እንዳሉት የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አመርቂ ናቸው፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሥርጭቱን ለመግታት እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ ሥርጭት ከደቡብ አፍሪካ ሞሮኮ እና ቱኒዚያ በመቀጠል በ4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። እስካሁንም 4 ሺህ 231 ያክል ዜጎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል።
በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት አማካኝነት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚደረጉ ጥናቶች ቫይረሱን ለመከላከል የሚኖራቸው ድርሻ ከፍተኛ መኾኑም ተጠቅሷል። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረዉም ተገልጿል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ በተደረገዉ ጥናት ላይ የሚደረገዉ ዉይይትም ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ታውቋል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ፣ ጠንካራና በማናቸውም የውጭ ተፅዕኖ የማይናወጥ ነው” የጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማዔል ኡመር ጉሌህ
Next articleባለፉት ዘጠኝ ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሥራ ዕድሎች መፈጠሩን የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ንጉሡ ጥላሁን ገለጹ፡፡