“በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ፣ ጠንካራና በማናቸውም የውጭ ተፅዕኖ የማይናወጥ ነው” የጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማዔል ኡመር ጉሌህ

301

“በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ፣ ጠንካራና በማናቸውም የውጭ ተፅዕኖ የማይናወጥ ነው” የጅቡቲ
ፕሬዝዳንት እስማዔል ኡመር ጉሌህ
ባሕር ዳር: ሰኔ 03/2013 ዓ.ም ( አሚኮ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፋይናንስ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የተመራና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የጦር ኃይሎች
ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ተመሥገን ጥሩነህን
ያካተተ የመንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማዔል ኡመር ጌሌህ ጋር ተገናኝተው በወቅታዊ
አካባቢያዊና በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት የሀገራቱ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ታሪካዊ፣ በማናቸውም የውጭ ኃይል ተፅዕኖ የማይናወጥ መሆኑ ተነስቷል።
የኢትዮጵያና ጅቡቲ የሕዘብ ለሕዝብ ትስስራቸውም በባህልና ቋንቋ ጭምር የተሳሰረና በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑም
ተመልክቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ለፕሬዝዳንቱ ማብራሪያ ሰጥቷል። በመንግሥት በኩል በሀገር ውስጥም ሆነ
ከውጭ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቋቋም የሀገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ እየተመራ መሆኑንና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም
በትግራይ ክልል የኅብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ድጋፎችንም አጠናክሮ የማስቀጠልና መደበኛ
የትምህርትና የግብርና ሥራዎችም እንዲጀምሩ የተደረገበት አግባብ መኖሩንም ተነስቷል፡፡
“በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በላይ የተጠናከረ መሆኑን ያነሱት የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማዔል
ኡመር ጌሌህ ግንኙነቱ ታሪካዊ፣ ጠንካራና በማናቸውም የውጭ ተፅዕኖ የማይናወጥ ነው” ብለዋል፡፡ ጅቡቲ ኢትዮጵያ የውስጥ
ችግሮቿን ለመፍታት እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቀዋል። በአንዱ ሀገር ውስጥ የሚፈጠር ችግር ሌላውም ላይ ተፅዕኖን
እንደሚያሳድር ፕሬዝዳንቱ በውይይቱ ወቅት አንስተዋል፡፡ የሀገራቱን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ጅቡቲ ከመቼውም ጊዜ በላይ
ዝግጁ መሆኗን ለልዑካን ቡድኑ አረጋግጠዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ኢታማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከጅቡቲው አቻቸው ጄኔራል ዘካሪያ ጋር
ተገናኝተው በሁለቱ የመከላከያ ኃይሎች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለው የሕዝብ ለሕዝብና የመንግሥታቱ ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ
ይህንኑ ግንኙነት በወታደራዊ መስክም ማስቀጠል እንደሚገባ ተወያዮቹ አንስተዋል፡፡ በዚሁ መሠረት በወታደራዊ መስክ የመረጃ
ልውውጥ፣ የትምህርትና ስልጠና ትብብር እንዲሁም የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በሀገራቱ የጋራ ድንበርና የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደርን ሰላማዊ ቀጣና ከማድረግ አኳያም በትብብር እንደሚሠሩ ተወያይተዋል።
በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ የጋር ሁለትዮሽ ውይይቶችንም አጠናክረው ለማስቀጠል ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ
ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየኢትዮ-አውሮፓ ሕብርት የጋራ ምክክር ተካሄደ።
Next articleየኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከግብዓት ማሟላት ጀምሮ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት አስታወቀ።