
በመጀመሪያ ምእራፍ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ
‘የዓለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ ‘ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚዎች ተናገሩ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 02/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ያገኘው ‘ዓለም አቀፍ ጥምረት
ለኢትዮጵያ’ ኩባንያ ሥራ ለመጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ትላንት ተፈራርሟል።
የስምምነት ፊርማው የተከናወነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኬኒያው ፕሬዝዳነት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት ነው።
የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ፤ ከቮዳኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሻሚል ጆሱ፣ ከሳሪ ኮም
ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒተር እንዲንግዋ እንዲሁም ከሲሚቶሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማይሽ ማሂሽታ ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
በጥምረት ጨረታውን ካሸኑፉት ኩባንያዎች መካከል 56 በመቶ ድርሻ ያለው የኬኒያው የሳፋሪ ኮም ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ፒተር እንዲንግዋ፤ አጠቃላይ የጨረታ ሂደቱ ግልጽና ተዓማኒ እንደነበር ተናግረዋል። በቀጣይ የመጀመሪያ ምእራፍ ሥራቸውም
በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እንደሚያተኩር ነው የጠቆሙት።
የሚያስፈልጋቸውን የሰው ኃይል ለማሟላትም ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ጋር በመቀራረብ የክህሎት ግንባታ ሥራ
እንደሚያከናውም ገልጸዋል።በዘርፉ ተዓማኒና ተፎካካሪ ለመሆን ዝግጁ ነን ሲሉም ነው የጠቆሙት።
ኢትዮጵያውያን የቢዝነስ አቅማቸውን በማጎልበት ለወደፊቱ የተሻለ ሥራ እንዲሠሩ እንደሚያግዙም አረጋግጠዋል።
የቮዳኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሻሚል ጆሱ በበኩላቸው በመጀመሪያ ምእራፍ ሥራቸው በርካታ የሀገሪቱን አከባቢዎች የሚሸፍን
ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቴሌኮም ኔትወርክ ማስፋፋት ላይ በስፋት መዋለ ንዋይ እንደሚያወጡ ተናግረዋል። በዚህም
ኢትዮጵያውያን በምናቀርባቸው የዲጂታል ‘ፕላትፎርሞች’ ተጠቅመው ምርቶቻቸውን በቀላሉ እንዲሸጡ በማድረግ ኑሯቸው
እንዲሻሻል እናደርጋለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
“ዓለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ” የኬኒያው ሳፋሪ ኮም፣ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎንና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካውን
ቮዳኮም፣ የጃፓኑን ሲሚቶምና ዲኤፍሲን በጥምረት የያዘ ኮባንያ ነው።
ኩባንያው ጨረታውን ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግሥት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለስልጣን መግለፁ
ይታወቃል።
ኩባንያው በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ ከ8 ቢለዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ገልጿል፤ በዚህም
ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m