የአማራ ልማት ማኅበር አልማና የክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ክልሉ የገቡ ዜጎችን ለማቋቋም ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡

196
የአማራ ልማት ማኅበር አልማና የክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ክልሉ የገቡ ዜጎችን ለማቋቋም ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ የአማራ ልማት ማኅበር አልማ ከክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር በመኾን በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫው እንደተመላከተው በተለያዩ ምክንያቶች ከ600 ሺህ ያላነሱ ዜጎች ተፈናቅለው በክልሉ ይገኛሉ።
በመግለጫው የአማራ ልማት ማኅበር አልማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መላኩ ፋንታ እንደገለጹት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ446 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በሰሜን ሸዋ 246 ሺህ ዜጎች መፈናቀላቸውና ከ3ሺህ በላይ ቤቶች መቃጠላቸውም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ነው የተባለው።
የአማራ ደን ልማት የቤት መሥሪያ እንጨት እየደገፈ እንደኾነ የተናገሩት አቶ መላኩ በቀጣይም ባለ ሃብቱ፣ድርጅቶች፣ ዲያስፖራውና ከክልሉ ውጭ ያለው ዜጋ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የተለያዩ የእርዳታ ማስገኛ ዘዴዎችን በማዘጋጀት የሃብት ምንጭ ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ እንደኾነም ተብራርቷል፡፡
ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የተቋቋመው ግብረ ኀይል 750 ሚሊዮን ብር ያሰባስባል ተብሎ ይጠበቃል። በገንዘብና በቁሳቁስ ለሚደግፉ እንደየፍላጎታቸው ማስተናገድ እንደሚቻልም ተጠቁሟል።
በተለይም በገጠርና በከተማ ምን አይነት ቤቶች ይሠራሉ የሚለው ፕላን ስለተዘጋጀ በማኀበርና በግል ቤት በስማቸው መሥራት ለሚፈልጉ ክፍት እንደኾነ አቶ መላኩ ገልጸዋል።
የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ በፊትም ዜጎችን ማቋቀቋም እንዲቻል ሁሉም ባለውና በቻለው መጠን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል። በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚደረግባቸው የባንክ ቁጥሮችም ይፋ ኾነዋል፡-
-ንግድ ባንክ 1000399788181
-አቢሲኒያ ባንክ 66956466
-አባይ ባንክ 2012117396084010
-ዳሽን ባንክ 5020809534011
-ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ 1079601001041
-ህብረት ባንክ 2210411629526018
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleልዩ ዓላማ ያላቸው የድጎማ ገቢዎች ላይ አሠራር ባለመዘርጋቱ ፍትሐዊ ያልሆነ የመልማት አዝማሚያ ስለሚፈጥር ሊታሰብበት እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡
Next article“ተውን ነጻነታችንን እናጣጥም” የሑመራ ነዋሪዎች