“ከ40 በመቶ በላይ ሕጻናት በምግብ ደኅንነት ችግር ይገጥማችዋል” የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

100
“ከ40 በመቶ በላይ ሕጻናት በምግብ ደኅንነት ችግር ይገጥማችዋል” የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስ እና የስነ-ምግብ ምርምር ዳሬክተር ዶክተር ማስረሻ ተሰማ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በጤና እና በምግብ ዘርፍ ከፍተኛ የአሠራር ለውጥ እየመጣ ነው፡፡ በምግብ ደኅንነት ዙሪያ በርካታ ችግሮች ይስተዋላሉ ያሉት ዳይሬክተሩ ከ40በመቶ በላይ ሕጻናት በምግብ ደኅንነት እንደሚጠቁ ገልጸዋል፡፡ ሕጻናትም ለመቀንጨር ችግር እንደሚጋለጡ ጠቅሰዋል፡፡
የምግብ ደኅንነት ችግር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ እያደረሰ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ሕጋዊ ያልሆነ ግብይት በዋናነት በኢትዮጵያ ከምግብ ደኅንነት ችግር ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ችግሮች መንስዔ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሠራበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ከምግብ ደኅንነት ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮችንም ለመቅረፍ በ24 ከተሞች በተደረገ ቅኝት የሚያስፈልጉ የገንዘብ ድጋፎችን በማድረግ በመሥራት ላይ እንደሚገኙም ዶክተር ማስረሻ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ የምግብ ደኅንነት የሁሉም አካል ኀላፊነት መሆኑን በመገንዘብ ለተግባራዊነቱ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡
የጤና ሚኒስተር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ የምግብ ደኅንነት ጉዳይ የኹሉም ሰው ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ምግብ ደህንነቱ የተጠበቀ ከሆነ ለመጪው ትውልድ ትርጉም ያለው በመሆኑ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስቀረት የቁጥጥር ስራ ላይ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
በምግብ ደኅንነት የቁጥጥር ተግባራት ላይ በግብርና ምርት እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ ሰፊ ሥራ መሥራት ስለሚጠይቅ በትብብርና በቅንጅት መፈጸም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የሕግ አካላት፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በምግብ ደኅንነት የቁጥጥር ተግባራት ላይ ትልቅ ሚና ስላላቸው የቁጥጥር ስራ ላይ አስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ ከኅብረተስቡ ጋር በጋራ በመሆን እንዲሠሩ መጠየቃቸውን ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበት ኬኒያ ታምናለች” የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሪይቸል ኦማሞ
Next articleበህወሃት የሽብር ቡድን አባላት ሀብቶች ላይ ተጨማሪ ጥቆማ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።