
የአማራ ክልል 3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በማስጀመሪያ መርኃግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የኦሮምያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
በአማራ ክልል በ2013 ዓ.ም ለሚከናወነው 3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 1 ነጥብ 83 ቢሊዮን ችግኝ ይተከላል።
እንደ ሀገር በዚህ ዓመት 6 ቢሊዮን ችግኝ በአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር ለመትከል ታቅዷል።
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር በአብዛኛው ሀገር በቀል ችግኝ እንደሚተከልም ታውቋል።
በአማራ ክልል በመጭው ሐምሌ 8/2013 ዓ.ም በአንድ ጀንበር ከ247 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
ዘጋቢ:- ስማቸው እሸቴ – ከደብረ ማርቆስ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m