የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በብልጽግና ፓርቲ የደላንታ ወረዳ ሕዝብን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሄዱ፡፡

421

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በብልጽግና ፓርቲ የደላንታ ወረዳ ሕዝብን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሄዱ፡፡

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገልጤና ከተማ የምረጡኝ ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው። አቶ ገዱ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ከውስጥ እና ከውጭ ጫናዎች በበረቱበት ወቅት የሚደረግ እንደመኾኑ ውስጣዊ አንድነት ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በጋራ በመኾን ለኢትዮጵያ ብልጽግና መረጋገጥ የበኩሉን መወጣት አለበት ያሉት አቶ ገዱ ሕዝቡ እውነተኛ አገልጋዮችን በመምረጥ ለምርጫው ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊነት መሥራት እንዳለበትም ተናግረዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤርሚያስ መኮንን ብልጽግና የተስፋ ፓርቲ ብቻ ሳይኾን ለወረዳው ነዋሪዎች ሁለንተናዊ ልማት መረጋገጥ የሚሠራ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ቤተልሔም ሰለሞን – ከደላንታ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወልድያ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳና ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ነው።
Next article“የዛሬው ትውልድ ኢትዮጵያን ከውጪም ከውስጥም ጠላት በመከላከል የጀግንነት ታሪኩን ዛሬም እንድትናንቱ እንዲደግም ጥሪ አቅርባለሁ” ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ