የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወልድያ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳና ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ነው።

305

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወልድያ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳና ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ነው።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሕዝባዊ ውይይቱ ላይ የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ረዳት ኘሮፌሰር ) “አብን ያነገበው ዓላማ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእኩልነት፣ በነፃነትና በፍትሐዊነት እንዲኖር ሥርዓት የሚዘረጋ ነው፤ አብን አጀንዳውም፣ ጥያቄውም የሕዝብ ነው” ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ በፍትሕ አደባባይ አንሶ እንዲታይ፣ ከኢትዮጵያ እንዲሳደድ ሲደረግ መኖሩን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ እንሠራለን ነው ያሉት፡፡

ፍትሕና እኩልነትን አስፍነን የአማራ ሕዝብ በልማት እኩል ተጠቃሚ እንዲኾን እንደሚሠሩ የአብን ሊቀመንበር ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል-ከወልድያ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአርሶ አደሮች ገቢ በሚያስገኙና ፈጥኖ በሚደርሱ ሰብሎች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ፡፡
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በብልጽግና ፓርቲ የደላንታ ወረዳ ሕዝብን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሄዱ፡፡