አርሶ አደሮች ገቢ በሚያስገኙና ፈጥኖ በሚደርሱ ሰብሎች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ፡፡

214

አርሶ አደሮች ገቢ በሚያስገኙና ፈጥኖ በሚደርሱ ሰብሎች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ፡፡

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራልና የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳን ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ የተካሄደው 01 ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች ገቢ በሚያስገኙና ፈጥኖ በሚደርሱ ሰብሎች ላይ በማተኮር ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ከውጭ የሚገባውን ምርት ለማስቀረት በተያዘው ሀገራዊና ክልላዊ አቅጣጫ መሰረት በዚህ ዓመት ስንዴን በመስኖ የማልማት ሥራ መጀመሩን የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ቃልኪዳን ሽፈራው ተናግረዋል።

በዘንድሮ የበጋ ወቅት በዞኑ በሚገኙ 11 ወረዳዎች ስንዴ በመስኖ እየለማ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ዞኑ ለመስኖ ልማት አመቺ በሆኑ በ35 ቀበሌዎች 1 ሺህ 100 ሄክታር ገደማ በመስኖ ስንዴ ማልማት መቻሉን ገልጸዋል። ከዚህም ከ36 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ነው መምሪያ ኀላፊው የተናገሩት፡፡

ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን – ከደላንታ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ግንብ ችግኝ ተከሉ፡፡
Next articleየአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወልድያ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳና ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ነው።