
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ግንብ ችግኝ ተከሉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ የደጅ አዝማች ብሬ ዘገዬ መታሰቢያ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የመሠረተ ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት ጎን ለጎን የችግኝ ተከላ መርኃግብር ተካሂዷል፡፡
በመርኃግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ፣ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ችግኝ ተክለዋል።
መሪዎቹ ችግኝ የተከሉት በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ግንብ ነው።
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m