ቀዳሚዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ትምህርት ቤት ግንባታ ሥራ አስጀመሩ፡፡

596

ቀዳሚዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ትምህርት ቤት ግንባታ ሥራ አስጀመሩ፡፡

ቀዳሚዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ትምህርት ቤት ግንባታ ሥራ አስጀመሩ፡፡

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ነው የደጅ አዝማች ብሬ ዘገዬ መታሰቢያ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የመሠረተ ድንጋይ ያስቀመጡት። የመሠረተ ድንጋዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀደማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ምክትል ጠቅላይ ሚነስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን፣ ርእስ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ነው ያስቀመጡት።

ቀደማዊት እመቤቷ በአማራ ክልል ከአሁን ቀደም አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አስገንብተው አስመርቀዋል። ትምህርት ቤቶቹ ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ባለፉት ሦስት ዓመታት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 20 ትምህርት ቤቶችን አስገንብተዋል። 16ዎቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሲሆኑ ቀሪ አምስት ትምህርት ቤቶች በግንባታ ላይ ናቸው።

የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቅርቡ የሚጀምሩ 7 አዳዲስ የትምህርት ቤት ግንባታ ይፋ አድርገዋል። ከሰባቱ ትምህርት ቤቶች አንዱ ዛሬ የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠለት የማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ የደጅ አዝማች ብሬ ዘገዬ መታሰቢያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንደኛው ነው።

ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ-ከማሰሮ ደንብ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየጣና በለስ ቁጥር አንድ ስኳር ፕሮጀክት እውነታዎች
Next articleብልጽግና ፓርቲ ያዘጋጀው የስድስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር በመስቀል አደባባይ ተካሄደ፡፡