“ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለዘላቂ አገራዊ ብልፅግና” በሚል መሪ መልዕክት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው::

122

“ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለዘላቂ አገራዊ ብልፅግና” በሚል መሪ መልዕክት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው::
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለዘላቂ አገራዊ ብልፅግና” በሚል መሪ መልዕክት የመለስ
ዜናዊ አመራር አካዳሚ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት በመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በሚኒስትር ድኤታ ማዕረግ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል
ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ ሽቱ፤ 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫን በሳይንሳዊ ትንታኔ የታገዘ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ መረጃን ለሕዝብ
ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው።
በአገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ ሒደት የሚደግፉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለመደገፍና ለማበረታታት የፓናል መድረኩ ከፍተኛ
እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡በመድረኩም ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባሕሪያትና ምነነት በኢትዮጵያ እና ዴሞክራሲያዊ
ምርጫና የባለድርሻ አካላት ሚና በኢትዮጵያ የሚሉ ጥናታዊ ጹሑፎች ቀርበዋል፡፡
ለውይይት ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባሕሪያትና ምነነት በኢትዮጵያ በሚል የመነሻ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት ዶክተር
ባዩልኝ ዘመድአገኝሁ በኩላቸው እንደተናገሩት፤ ምርጫ የዴሞክራሲያዊነት የመጨረሻ ግብ አለመሆኑን ጠቅሰው ነፃ የመወዳደሪያ
ሜዳ፣ሁሉንም ያሳተፈ፣ ፍትሃዊ፣ ግልፅና ተጠያቂነት ሊኖረው ይገባል።
ይህ እንዲሆን ለማስቻል ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁሶችን በማሰራጨትም ሆነ ፣ መገናኛ ብዙኋን ፍትሃዊ ዘገባውን በማካሔድ
ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የፍትሕ አካላት ተወካዮች፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት፣ የሲቪክ ማሕበራትና የሚዲያ ሃላፊዎች፣ ተፎካካሪ
ፓርቲ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰቡ ክፍሎቸ እየተሳተፉ ነው፡፡
የምርጫው ባለድርሻ አካላት በምርጫው ጊዜም ሆነ ከምርጫው በኋላ ሚናቸውን በመወጣት የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት
ማረጋገጥ እንዳለባቸውም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ዘገባው የኢፕድ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበሕግ ማስከበር ግዳጅ የላቀ አፈፃፀም ላላቸው የአየር ኃይል አባላት የዕውቅና ሽልማት እና ማዕረግ የማልበስ መርሐ-ግብር ተካሄደ።
Next articleአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተደራሽነቱን ከማስፋት ባለፈ የዜናና ፕሮግራም አቀራረብ ማሻሻያዎችን እያከናወነ ነው።