በሕግ ማስከበር ግዳጅ የላቀ አፈፃፀም ላላቸው የአየር ኃይል አባላት የዕውቅና ሽልማት እና ማዕረግ የማልበስ መርሐ-ግብር ተካሄደ።

214

በሕግ ማስከበር ግዳጅ የላቀ አፈፃፀም ላላቸው የአየር ኃይል አባላት የዕውቅና ሽልማት እና ማዕረግ የማልበስ መርሐ-ግብር ተካሄደ።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የሕወሓት ጁንታ ላይ መንግሥት ባስቀመጣው አቅጣጫ መሠረት ሕግን የማስከበር ግዳጅ ላይ በላቀ ወታደራዊ ዝግጁነት እና ጀግንነት ፈፅመው የተመለሱ በኢፌዴሪ አየር ኃይል የምሥራቅ አየር ምድብ አባላት የጀግና አቀባበል ከማድረግ ባለፈ የዕውቅና ሽልማት እና ማዕረግ የማልበስ መርሐ-ግብር ተካሄዷል።

በኢፌዴሪ አየር ኃይል የምሥራቅ አየር ምድብ በበጀት ዓመቱ በግዳጅ አፈፃፀም፣ በፈጠራ እና ሞዲፊኬሽን፣ በሥልጠና፣ በወታደራዊ ዲሲፒሊን፣ በመልካም አስተዳደር ግንባታ ውጤታማ በሆነ መልኩ ላከናወኑ ዩኒቶች አካላት እና ሠራተኞችም የምስጋና እንዲሁም ዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢፌዴሪ አየር ኃይል እና ሠራዊት አባላት ግዳጅ ሰፊ ከመሆኑ ባለፈ በርካታ ሥራዎች እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

አሁን ላይ የተጀመሩትን አጠቃላይ የምድቡን ዝግጁነት በማረጋገጥ ሠራዊቱን ለማንኛውም ግዳጅ ማዘጋጀት ይገባል ሲሉም አክለዋል።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ተዋጊ የአየር ምድቦች አንዱ በሆነው ምሥራቅ አየር ምድብ ባለፉት 3 ዓመታት ተቋማዊ ሪፎርሙ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ “ሠራዊት ሀገር እንጂ ብሔር የለውም” በሚል መሪ ቃል በተሠራው የሠራዊት ግንባታ ሥራ አበረታች ውጤት መገኘቱን በኢፌዴሪ አየር ኃይል የምሥራቅ አየር ምድብ አዛዥ የሆኑት ኮረኔል አበበ ለገሰ ተናግረዋል።

በዚህም ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወገንተኝነት፣ ከብሔርተኝነት እና ከዘረኝነት አመለካከት በፀዳ መልኩ ተልእኮውን በላቀ ጀግንነት የሚፈፅም ጠንካራ ሠራዊት መገንባቱን ነው የገለጹት።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ፣ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ በኢፌዴሪ አየር ኃይል የምሥራቅ አየር ምድብ አመራር እና አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳታፊ መሆናቸውን ከድሬዳዋ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የባሕር ዳር ከተማ የጽጥታ መዋቅር አስታወቀ።
Next article“ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለዘላቂ አገራዊ ብልፅግና” በሚል መሪ መልዕክት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው::