ኮሚሽኑ ከ700 ሺህ ኩንታል በላይየምግብ ድጋፍ ወደ ትግራይ መላኩን አስታወቀ።

162

ኮሚሽኑ ከ700 ሺህ ኩንታል በላይየምግብ ድጋፍ ወደ ትግራይ መላኩን አስታወቀ።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የብሄራዊ አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እስካሁን ባለው ለትግራይ ክልል 772 ሺህ 954 ኩንታል እህልና 289 ሺህ 339 ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች ሶስተኛ ዙር ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን ገልጿል፡፡

ድጋፉ በመንግሥትና በዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዲሁም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ጥምረት እየተሰጠ መሆኑም ነው የተገለፀው።

ካለፈው ወር አንስቶ በትግራይ ክልል የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ ከክልሉ የቆዳ ስፋት 86 በመቶ የሚሆነው በአጋር አካላት እንደሚሸፈን እና ቀሪው 14 በመቶ ደግሞ በመንግስት እንደሚሸፈን መገለፁ ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት ምዕራብ ዞን፣ ደቡብ ዞን አምስት ወረዳዎች፣ አላማጣ ከተማ፣ አላማጣ ዙሪያ ወረዳ፣ ኦፍላ ወረዳ፣ ኮረም ከተማ እና ዛታ ወረዳ በመንግስት የሚሸፈኑ ሲሆን ደቡብ ዞን ሶስት ወረዳዎች፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ እና የመቀሌ ከተማ ደግሞ በአጋር አካላት የሚሸፈኑ መሆናቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢዜአ እንዳሉት ከትግራይ በተጨማሪ ኮሚሽኑ በአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችም ጊዜያዊ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል በማቋቋም እየሰራ ነው።

ማስተባበሪያ ማዕከሉ መረጃን ለመሰብሰብና መረጃውን መሰረት በማድረግ ሊሰጥ የሚገባውን ድጋፍ በተገቢው መልኩ ለማድረስ የሚያስችል መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

እንደ ብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እስካሁን ድረስ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 124 ሺህ 49 ኩንታል እህል የተጓጓዘ ሲሆን በአማራ ክልል ለአጣዬ ተፈናቃዮችም 32 ሺህ 520 ኩንታል እህል ተልኳል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዘመናዊ የፎረንሲክ ሰነድ ማጣሪያ ላቦራቶሪ ስራ ጀመረ።
Next articleየአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በውጭ ሀገራት የማሰራጫ ስቱዲዮ እንዲኖረው ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ሙሉቀን ሰጥዬ ገለጹ።