
የጸጥታ ኀይሉ ከሕብረተሰቡ ጋር ተባብሮና ተቀናጅቶ የባንዳዎችን እኩይ ድርጊት እየቀለበሰ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በቀጣይ የድርጊቱ ተሳታፊዎች እና የደረሰውን ጉዳት ጥልቅ ምርመራ በማድረግ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑንም ገልጿል።
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ)
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ ሙሉ መግለጫ ቀጥሎ ይቀርባል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የክልሉን ብሎም የሀገራችን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ተቋሙ የህዝብ የሰላምና ደህንነት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚያስችል መልኩ የመዋቅርና የሰው ሀይል ስምሪት ማስተካከያዎችን ከማድረጉም በላይ ለአሰራር ያስቸግሩ የነበሩ ነባር ደንብና መመሪያዎችን አሻስሏል እያሻሻለም ይገኛል፡፡
ከመሰረቱ የአማራ ህዝብን እንደ ጠላት ቆጥሮ መዋቅራዊ ጭቆናና ግፍ ሲያደርስ የነበረው አሸባሪው የህዋት ቡድን ከአራት ኪሎ ከተባረረ ጀምሮ በግልፅና በስውር በክልላችንና በህዝባችን ሲያደርስ የነበረው ያለተቋረጠ ግፍ ወደ ለየለት ግልፅ ማጥቃት ሲሸጋገር ተቋሙ ለጊዜው የሚመጥን ዝግጅት በማድረግ ተገቢውን አማራር ሰጥቶ ጥቃቱን በሚገባ መክቷል፡፡
አሸባሪው ቡድን ሀገርን ክዶና ደፍሮ በማዋረድ የተላለፈውን ቀይ መስመር ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት መክቶ የሀገር ባለውለታነቱን አስመሰድክሯል፡፡
ከዚህም ባሻገር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የወንጀል መከላከል ስራዎችን በሁሉም አካባቢዎች ተግባራዊ በማድረግ በአንፃራነት የተረጋጋ ክልል ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡፡
የለውጥ ስራ ሂደት ነው፤ በአንድ ጀንበር የሚቋጭ አይሆንም ገና ህዝባችን ያላረካነው ያአገልግለት አሰጣጥ ጉድለቶች ያሉብን ከህዝባችን ጋራ በመሆን ወደ ፊት የተሻለ አገልግሎት አሰጣጣችን እንዲኖር የለውጥ ስራውችን እየሰራን እንገኛለን፡፡
ይሁን እንጂ ክልሉን ለመወጠር ከውስጥ እስከ ውጭ ተናበው የሚሰሩ ሀይሎች የሚያደርሱት ተደጋጋሚ ጥፋት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በሰሜን ሽዋ አጣየ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አካባቢ፤ በቅርቡም የቅማንት ፀንፈኛ ቡድን በተደራጀ መንገድ በጎንደር ከተማ ላይ አስቦት የነበርው ድርጊት የህዝባችን ሰላም ለማናጋት የክልሉን ሰላም የማደፍረስ ተልዕኮ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡
ዛሬም እንደ ትናንቱ የፀጥታ ሀይላችን ከህብረተሰቡ ጋር ተባብሮና ተቀናጅቶ የባንዳዎችን አኩይ ድርጊት የቀለበሰ ሲሆን በቀጣይ የድርጊቱ ተሳታፊዎች እና የደረሰውን ጉዳት ጥልቅ ምርመራ በማድረግ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ተቋማችን በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ለሰላም ወዳድ ህዝባችን ልናረጋገጥን እንወዳለን፡፡
የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራር ያለፉና የቀጣይ ሁኔታዎችን በመገምገም የቀጣይ የቀሪ ወራት ቁልፍ ተግባራትን ለይቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ የተቋሙ አሰራሮችን በመፈተሸና ችግሮችን ለይቶ ለመደገፍ በተለይም 6ኛው አገረ አቀፍ ምርጫ በክልችን ያለምንን የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ የፖሊስ ሀይሉ ገለልተኝነት ያረጋገጥ ዕቅድና ስምሪት ተሰጥቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ለዚህም የመረጃና ደህንነት ስራዎችን በማጠናከር ከአጎራባች ክልሎች፣ ከፌድራል የፀጥታ ተቋማት፣ ከብሄራዊ ደህንነት ጋር በትብብር እየተሰራ ሲሆን በአጠቃላይ በክልሉ የህግ የ በላይነትን በማረጋገጥ በቅድመ መከላከል ላይ የተመሰረተ ፖሊሳዊ ተግባራትን ለመከወን በምናደርገው ጥረት ህብረተሰቡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከጎናችን እንዲሰለፍ ጥሪ እናቀርባለን።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m