መገናኛ ብዙሃን እየጨመረ የመጣውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚመጥን የሳይበር ደኅንነት እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

120
መገናኛ ብዙሃን እየጨመረ የመጣውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚመጥን የሳይበር ደኅንነት እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተመላከተ፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) መገናኛ ብዙሃን እየጨመረ የመጣውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚመጥን የሳይበር ደኅንነት እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ይግዛው ገለጹ።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ጋር በተባበር ለሚድያ ባለቤቶችና ባለሞያዎች የሳይበር ደኅንነትን አስመልክቶ ውይይት እያደረገ ነው፡፡ መገናኛ ብዙኀን እየጨመረ የመጣውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን የሚመጥን የሳይበር ደኅንነት እውቀት አለመኖሩ በውይይቱ ተመላክቷል፡፡
የኢንፎርሚሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹሜቴ ይግዛው እንዳሉት ሚዲያዎች ቴክኖሎጂን የመጠቀምና መረጃን በጥራትና በፍጥነት የማድረስ አቅም እያደገ ቢመጣም ይህን የሚመጥን የሳይበር ደኅንነት ክህሎት አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ ባለፉት ሦሥት ዓመታት በርካታ ሀገራዊ ሪፎርሞች ማድረጓን ተከትሎ በርካታ የሳይበር ጥቃት መሰንዘራቸውን አስታውሰው፤ በመጪው ወራት የሚደረገው ሀገራዊ ምርጫና ሁለተረኛው ዙር የህዳሴ ግድብ ውኃ ሙሌትን ተከትሎ ሊሰነዘሩ የሚችሉ የሳይበር ጥቃትን ለመመከት ለሚዲያ ባለሞያዎች ግንዛቤ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው ሚዲያዎች የሚያሰራጩት መረጃ ተዓማኒነቱን ከመጠበቅ ባለፈ ለሳይበር ደኅንነት ትኩረት እና እውቀት መኖር አስገዳጅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ በወቅታዊ ጉዳዮች የሳይበር ደኅንነትና የመገናኛ ብዙኀን ሚና በሚል የተዘጋጀ ሰነድ ለተሳታፊዎች በመቅረብ ላይ መሆኑን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበወልድያ ከተማ የተጀመረው የከፍተኛ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ፡፡
Next articleየወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡