በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የጉዞና ተያያዥ ማዕቀብ በመቃወም በካልጋሪ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

107
በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የጉዞና ተያያዥ ማዕቀብ በመቃወም በካልጋሪ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በካናዳ አልበርታ ግዛት በካልጋሪ፣ ሌትብሪጅና ፎርትማክመሪ የሚኖሩ ኢትዮ – ካናዳውያን የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የጉዞና ተያያዥ ማዕቀብ በመቃወም በካልጋሪ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡
ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ በትግራይ ክልል አሸባሪው ህወሃት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታ ላይ ያደረሰውን ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ ተከትሎ መንግሥት የወሰደውን የሕግ ማስከበርና ወንጀለኞቹን ለሕግ የማቅረብ ሕጋዊ ርምጃ የሚደግፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአሜሪካን መንግሥት እውነታውን በትክክል ሳይመረምር በተሳሳተና እውነትን መሠረት ባላደረግ ሁኔታ የኢትዮጵያን መንግሥት ከአሸባሪዎች እኩል በመመልከት ማዕቀብ መጣሉ ስህተት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ሰልፈኞቹ በመልዕክታቸው ወቅቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የዜጎቿን ድጋፍ የምትፈልግበት ጊዜ መሆኑን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለምንም የሃይማኖት፣ የብሔርና የፆታ ልዩነት በአንድነት በመቆም ድጋፉን ማድረግ እንዳለበት፣ አሜሪካም ሆኑ ሌሎች ምዕራባውያን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ የሚፈልጉት ሀገሪቱ ደሃ በመሆኗ መሆኑን፣ መንግስት ሃገሪቱዋን ከድህነት ለማውጣት የሚያደርገውን ጥረት በተለያየ መንገድ እንደሚደግፉና ከዚህ ጋር ተያይዞ ወደ ኢትዮጵያ የሚልኩትን ገንዘብ በህጋዊ መንገድ ብቻ እንደሚልኩ አረጋግጠዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘለበት መርሃ ግብር መሠረት ሙሊቱ እንዲካሄድና ፕሮጄክቱም እንዲጠናቀቅ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ፣ በተመሳሳይ የሀገራቸው የካናዳ መንግሥትም በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ እንዲቀጥል እንዲደግፍና አላስፈላጊ ጫና ኢትዮጵያ ላይ ከማሳረፍ እንዲቆጠብ ጠይቀዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከወጣት እስከ አዋቂ የተሳተፉ ሲሆን፣ የተለያዩ መልዕክቶችም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ቀርበዋል፡፡
በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በሀገራቸው ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገው ጫና እስካልቆመ ድረስ ተመሳሳይ ዝግጅቶችን በሰፊው ለመቀጠልና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጽ ለመሆን ቃል መግባታቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይዋን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሷ ለመፍታት እያደረገችው ያለውን ተግባር እንደምትደግፈው ኩባ ገለጸች።
Next articleሕጋዊ እውቅና ለተሰጣቸው የሲቪክ ማኅበረሰብ ተቋማት የመራጮች ትምህርት ሲሰጡ የጸጥታ አካላትም ሆኑ ባለድርሻ አካላት ትብብር ማድረግ እንደሚገባቸው ምርጫ ቦርድ አሳሰበ፡፡