
በኖርዌይ ኦስሎና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኖርዌይ ኦስሎና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በጋራ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ላይ ኢ-ፍትሐዊ በሆነ ሁኔታ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም በኦስሎ የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።
በኖርዌይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ ደስታ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ጣልቃ ገብነትና ከሉዓላዊነት ጋር የሚፃረር አደገኛ አካሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የተሳሳተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋን እያራመደች በመሆኑ ይሄንኑ በአፋጣኝ እንድታሻሽል፣ የአሜሪካ ሴኔት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ላይ በአሸባሪው ሕወሓት በሚነዛው የተሳሳተ መረጃ ላይ በመመርኮዝ ያስተላለፈውን ውሳኔ ያለቅድመ ሁኔታ እንዲነሳ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል፡፡
ሰልፈኞቹ የአሜሪካ መንግሥት በሀገራቱ ጉዳይ ላይ እያሳደረ ከሚገኘው ጫና እንዲቆጠብ የተፃፈ የተቃውሞ ደብዳቤ ኦስሎ ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ማስረከባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
