በኢትዮጵያ ላይ እየተሰነዘሩ ያሉ ያልተገቡ ጫናዎችን ለመመከት እንደሚሰሩ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ።

110
በኢትዮጵያ ላይ እየተሰነዘሩ ያሉ ያልተገቡ ጫናዎችን ለመመከት እንደሚሰሩ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ።
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ላይ እየተሰነዘሩ ያሉ ያልተገቡ ጫናዎችን ለመመከት እንደሚሰሩ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገልፀዋል::
በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ እና 500 ተሳታፊዎች የተገኙበት “ኢትዮጵያ በአዲስ መንገድ ላይ” የሚል መሪ ቃል የያዘ ውይይት ተካሂዷል፡፡
አምባሳደር ፍጹም አረጋ በውይይቱ ላት ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ፈተናዎች ለማክሸፍ በአገር ውስጥም በውጭም ያለው ኢትዮጵያዊ በተቀናጀ መልኩ እንዲረባረብ ጥሪ አድርገዋል፡፡
የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በበኩላቸው “አሁን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈቱብን ዘመቻዎች በራሳችን አቅም ከምንገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር የሚያያዙ መሆናቸውን ገልጸው ይህን የአገር አርማ ፕሮጀክት ተባብሮ ማጠናቀቅ ብዙዎችን ጫናዎች እንደሚቀንሳቸው ተናግረዋል፡፡
የግንባታ ሂደቱ 80 በመቶ ለደረሰው ይህ ታላቅ ግድብ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
መጪውን ምርጫ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የምርጫ ቦርድ የኮሚዩኒኬሽን አማካሪ ወ/ ሪት ሲሊያና ሽመልስ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቦርዱ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ከአሁን ቀደም ከነበሩት ምርጫዎች በተለየ ቦርዱ ከፍተኛ በጀት ከመንግስትም ከለጋሽ አገራትና ድርጅቶች አግኝቶ ለምርጫው ስኬታማነት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ብምርጫው 200 የግል ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉብት ገልጸው ይህም ካለፉት ምርጫዎች ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ የተሳተፉ የማህበራት አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊዎችም ከአገር ውስጥም ከውጭም የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም ለማናጋት እየሰሩ ያሉትንና ያልተገባ ጫና እያደረጉ ያሉትን ኃይሎች ከምንጊዜውም በላይ እንደሚታገሏቸው ቃል ገብተዋል፡፡
በተለይም የኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበር እና እየተሰነዘረ ያለውን ያልተገባ ጫና ለመቋቋም በተደረጃ መልኩ መንቀሳቀስ አስፈላጊ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአዲስ ዘመን ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።
Next articleበኢትዮጵያ ላይ የውጭ ኃይሎች እያደረጉትን ያለውን ጣልቃ ገብነትና ጫና ለመመከት እንደሚሠሩ በጣልያን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ፡፡