በአዲስ ዘመን ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።

141

በአዲስ ዘመን ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሊቦ ከምከም ወረዳ እና የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል። በአዲስ ዘመን ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወር በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ አርሶ አደሮች፣ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ ፈረሰኞችና አሽከርካሪዎች ተሳትፈውበታል።

ፓርቲው እጩዎችንም አስተዋውቋል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ መልዕክ ያስተላለፉት የጥረት ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስኪያጅ ባምላኩ አስረስ (ዶክተር) በመጪዎቹ ወራት የህዳሴ ግድብ ኹለተኛ ዙር ውኃ ሙሊት የሚከናወንበት እና ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚካሄድበት መሆኑን ጠቅሰው “ሀገራችንን ወደ ከፍታ ማማ የምናወጣበት ስለሆነ ብልጽግና ደፋ ቀና በማለት ላይ ነው” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍታ ያላስደሰታቸው የውስጥና የውጪ ኃይሎች ይህንን ልማት እና ሰላም ለማደናቀፍ በመረባረብ ላይ ስለኾኑ የአማራ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን በመሆን በድል እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፈንታ ማንደፍሮ (ዶክተር) ኢትዮጵያ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎች ውጥረት ውስጥ መሆኗን በሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አስገንዝበዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኹለተኛ ዙር ውኃ ሙሊትን ለማደናቀፍ እና ሀገሪቷን ለማፍረስ የሚታትሩ ኃይሎች እንዳሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

“ኢትዮጵያን በደማቸው ጠብቀው ያቆዩአት የጀግኖቹ ልጆች ነንና እኛም አስፈላጊውን መስዋእትነት ከፍለን የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት እናስጠብቃለን” ብለዋል።

የተጀመሩት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው፣ ሀገሪቱ የተጋረጠባት አደጋ ተወግዶ በሰላምና በእድገት ጎዳና እንድትራመድ ሕዝቡ ብልጽግናን እንዲመርጥ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ፡- ዋሴ ባየ – ከአዲስ ዘመን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየአማራ ሚደያ ኮርፖሬሽን የሚዲያ ተደራሽነትን ለማሳደግ እየሠራ ነው።
Next articleበኢትዮጵያ ላይ እየተሰነዘሩ ያሉ ያልተገቡ ጫናዎችን ለመመከት እንደሚሰሩ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ።