የኢትዮጵያ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ሊሻሻል ነው፡፡

301

የኢትዮጵያ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ሊሻሻል ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ
ደንብ ሊሻሻል ነው።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ክፍያ ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያ የዳኝነት የክፍያ ማሻሻያ ደንብ ከ68 ዓመት
በላይ ያስቆጠረ ነው። ደንቡ ፍርድ ቤቶች ለሚሰጡት አገልግሎት ተመጣጣኝ ገቢ እንዳያገኙ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
ክፍያው ወቅቱን ያላገናዘበ በመሆኑ አገልግሎቱን ለማሻሻል፣ መሰረተ ልማቱን ለመገንባትና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱ እንዳያድግ
አድርጓልም ብለዋል። በመሆኑም አሁን የተሻሻለው ረቂቅ ደንብ የኅብረተሰቡን የመክፈል አቅምና ወቅታዊ የዋጋ ግሽበት ባገናዘበ
መልኩ መሆኑን አስረድተዋል።
የቀደመው የአገልግሎት ክፍያ ደንብ ከፍርድ ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ ለመውሰድ ሃምሳ ሳንቲም ይጠይቃል፡፡ ይህ ክፍያ
በአሁኑ ወቅት ያለውን የአንድ የወረቀት ሂሳብ እንኳን የማይሸፍን መሆኑን ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል።
በፍርድ ቤቶች እየመጡ ያሉ ጉዳዮች ውስብስብና ሰፊ በመሆናቸው ይህንን መሸፈን የሚያስችል ገቢ ስለሚያስፈልግ የማሻሻያ
ረቂቁ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።
ለመጨረሻ ጊዜ ዛሬ ለውይይት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ታክሎበት በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት እንደሚቀርብ ፕሬዝዳንቷ ገልጸዋል።
የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በዓለም አቀፍ ተሞክሮ የተቃኘና የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብለዋል።
ፍርድ ቤቱ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ በርካታ የለውጥ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ
ደንብ የዚህ አንዱ አካል መሆኑም ተጠቁሟል።
አዲሱ ረቂቅ ደንብ በአገልግሎቶች ተመጣጣኝ የዳኝነት ክፍያን እንዲኖር፣የዳኝነት ክፍያን ፍርድ ቤቶች እንዲያስተዳድሩትና
ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲኖር ያስችላል መባሉን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“የተለያዩ የመሠረተ ልማት የሌለባቸው አካባቢዎች ቢገጥሙም ከኅብረተሰቡ ስለማይበልጡ ሳንታክት ልናገለግል ይገባል” የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የህክምና ዶክተሮች
Next article“በውስጣዊ ጉዳዮች ወሳኞች እኛ ኢትዮጵያውያን እንጂ ሌላ የውጭ ኃይል አይሆንም፤ ዕድሉም አይሰጠውም” የአዲስ አበባ ወጣቶች እና በጎ ፈቃድ ማስተባባሪያ ቢሮ ኀላፊ አብርሃም ታደሰ