“ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስራ ፈጠራ የምትመች ሀገር ለመፍጠር በልዩ ትኩረት እየሠራ ነው” የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

143
“ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስራ ፈጠራ የምትመች ሀገር ለመፍጠር በልዩ ትኩረት እየሠራ ነው” የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስራ ፈጠራ የምትመች ሀገር ለመፍጠር መንግሥት በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ደርጅቶች ( tech startups) እና ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን በቀላሉ ወደ ገበያ እንዲያስገቡ የሚያስችላቸውን ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
አይስ አዲስ (Iceaddis) የተሰኘውና ለጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሚሰራው ድርጅት 10ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡
የአይስ አዲስ መስራችና ሥራ አስኪያች አቶ ማርቆስ ለማ ድርጅቱ ለ163 የሥራ ፈጣሪዎችና ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ምቹ ሃሳባቸውን እንዲያበለፅጉና ወደ ገበያ እንዲገቡ የመሰረት ድንጋይ መጣል መቻሉን ተናግረዋል።
በቀጣይ ለጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ( tech startups)፣ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች፣ ለቴክኖሎጂ አልሚዎች የመስሪያ ቦታ በማመቻቸትና ስልጠና በመስጠት ለጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ምቹ ከባቢ ሁኔታን ለመፍጠር እንሠራለን ብለዋል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ አህመዲን መሃመድ (ዶክተር) አይስ አዲስ የመንግሥት ቢሮክራሲ ለቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዎች ምቹ ባልሆነበት ወቅት ተመስርቶ ውጤት ማምጣቱን አድንቀዋል፡፡
ይህንን ችግር በመረዳት መንግሥት ለዘርፉ ጀማሪ የሥራ ፈጣሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በልዩ ትኩረት እየሠራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ውስጥ የተካተቱ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
የቴሌኮም ዘርፍ ማሻሻያ ሥራን ጨምሮ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ፀድቆ ወደ ሥራ መግባት፣ የጀማሪ ቴክኖሎጂ ድርጅቶች አዋጅ መዘጋጀት፣ የኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ዝውውር አዋጅ መፅደቅ፣ የዲጂታል መታወቂያ፣ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትና ኢኮሜርስ ላይ በትኩረት እየተሠራ ስልመሆኑ አብራርዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው እዮብ ተካልኝ (ዶክተር) በአንድ ተቆጣጣሪ ብቻ ተይዞ የነበረውን የቴሌኮም ዘርፍ ወደ ግል የማዛወር ሂደት ውድድርን በመፍጠር ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ምቹ ከባቢ ሁኔታን ፈጣሪ የሆነው አይስ አዲስ 10ኛ ዓመት በዓሉ ላይ በዘርፉ ያሉ ችግሮችና የወደፊት ምቹ ሁኔታዎች ላይ የተመለከቱ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ መረጃው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleለፋሲል ከነማ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
Next articleበሞጣ ከተማ አስተዳደር የተጠናቀቁ መሰረተ ልማት ግንባታዎች ተመረቁ።