
በአጣዬ እና አካባቢው ለመልሶ ማቋቋምም 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 16/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት
የተቋቋመው ግብረ ሃይል ዛሬ በሰሜን ሸዋ የደረሰውን ጉዳት ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ሪፖርቱን ያቀረቡት ጉዳቱን ለማጣራት እና መልሶ
ለመገንባት የተቋቋመው የቴክኒክ ግብረ ኃይል ምክትል ሰብሳቢ ብርሃኑ ዘውዱ ናቸው።
በአጣዬ እና አካባቢው በተፈጸመው ጥቃት በሰሜን ሸዋ ዞን ብቻ 281 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በ197 ሰዎች የአካል ጉዳት
መድረሱን የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አጣሪ ግብረ ኀይል አስታውቋል። ግብረ ኀይሉ እንደገለጸው 3 ሺህ 73
ቤቶች የወደሙ ሲሆን 1 ሺህ 787 ሄክታር አዝርእት እና ቋሚ ተክል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
በቀጣይ ድጋፉ በሚደረግበት እና የተጠቃለለ የጉዳት ሪፖርት በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እየተገመገመ ነው። ለጠቅላላ መልሶ
ማቋቋምም 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሏል።
በቀጣይ የኦሮሚያ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንን በመገምገም ሪፖርት እንደሚቀርብም ተገልጿል።
የደረሰው ጥቃት ለበርካቶች ህይወት ማለፍ፣ መቁሰል እና ለንብረት መውደም እንዲሁም ለሥነ ልቦና ጉዳት ዳርጓል። በደረሰው
ጉዳት 246 ሺህ 818 ሰዎች ተረጅ ሆነዋል። በአጣዬ ብቻ 1 ሺህ 529 ቤቶች ወድመዋል። በተጨማሪም አራት ትምህርት
ቤቶች፣ 3 ጤና ጣቢያዎች ወድመዋል፡፡ 23 ሺህ ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከመጠጥ ውኃ አገልግሎት ውጭ አድርጓል። ሕዝብ
አገልግሎት የሚያገኝባቸው መንግሥታዊ ተቋማት ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ ወድመዋል፡፡ በአጣዬ ከተማ ሙሉ በሙሉ ጉዳት
ደርሷል። 7 የሃይማኖት ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች ደግሞ 11 ሆቴሎች፣ የእህል መጋዘን፣ 350 ሱቆች እና 43 ወፍጮ ቤቶች
ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በተጨማሪም 61 የአርሶ አደሮች የውኃ ፓምፕ (ጀኔሬተር) ሲወድሙ 582 እንስሳት ደግሞ እንደተዘረፉ ተገልጿል። በዚህም 237
ሺህ 157 ሰዎች ከመጠለያ ውጭ እና 9 ሺህ 661 ሰዎች በመጠለያ ውስጥ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
አካባቢውን መልሶ ለሟቋቋም የፈረሱ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የተለየ ዲዛይን እና የቤት አሠራር መከተል ያስፈልጋል ተብሏል።
ለመልሶ ማቋቋም በአርሶ አደሮች አካባቢ የእንስሳት እና የእንስሳት ህክምናን መልሶ ለመገንባት 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር
እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
• የመንግስት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት 162 ሚሊየን ብር ገደማ ያስፈልጋል ነው የተባለው።
• የግል ንግድ ቤቶችን እና አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት 107 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ይጠይቃል
• ትምሀርት ቤቶችን ለመገንባት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር
• የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት 18 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ያስፈልጋል
• ለጠቅላላ መልሶ ማቋቋም 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተብሏል።
ዘጋቢ፡- አንዷለም መናን- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m