የአማራ ሕዝብ የተጋረጡበትን ችግሮች ከሕዝብ ጋር በመተባበር ለመፍታት እንደሚሠራ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ገለጸ፡፡

527

የአማራ ሕዝብ የተጋረጡበትን ችግሮች ከሕዝብ ጋር በመተባበር ለመፍታት እንደሚሠራ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳውን በደሴ ከተማ አካሂዷል፡፡ በፓርቲዉ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተገኙት ደጋፊዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ አብን ምርጫውን ቢያሸንፍ ለወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር ምን አይነት የተለየ አሠራር ይዞ ይመጣል? አማራ ላይ እደረሰ ያለዉ ግፍ እና መፈናቀል እንዲቆም ምን ለማድረግ አቅዷል? የአማራ ሕዝብን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ምን ለመሥራት አስቧል የሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር እና የፓርቲዉ የምርጫ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ የሱፍ ኢብራሂም ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ የተጋረጡበትን ችግሮች ከሕዝብ ጋር በመተባበር ለመፍታት አብን እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

በአማራ ላይ ማንነትን በመለየት የሚፈፀም ሞት እና መፈናቀል ፓርቲው እንደሚያወግዘውም አመላክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የኹላችንም ሀገር ናት ያሉት አቶ የሱፍ አማራ መብቱ ተከብሮ እንዲኖር አብን እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡

በተለይ ባለፉት 30 ዓመታት የአማራ ሕዝብ በደል እና እንግልት ሲደርስበት ቆይቷል ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ ወጣቶች በሀገራቸዉ ሠርተው መለወጥ የሚችሉበት አማራጭ ስትራቴጂ መቀየሱን ገልጸዋል፡፡ በምርጫ ቢያሸንፉ ወጣቶች ኹሉን አቀፍ ተጠቃሚነታችው ከፍ እንዲል እንሠራለን ብለዋል፡፡

የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የመሠረተ ልማት ችግሮችን በመፍታት እንደሚሠራ አንስተዋል፡፡ በተለይም ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በከተሞች እና በገጠር የሚስተዋለውን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ ውጭ ሀገር ከሚገኙ ከተሞች ጋር ትብብርን በማጎልበት እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አንዋር አባቢ – ከደሴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleወልቃይት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለኹለተኛ ጊዜ ያስለጠናቸውን 86 ተማሪዎችን አስመረቀ።
Next articleበትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ እና መልሶ ማቋቋም ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡