
“አሸባሪው ሕወሃት በመወገዱ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በስሙ የተነገደበት የትግራይ ሕዝብም ነፃ ወጥቷል”
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዋና አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለሕዝብ ማንነት መከበርና ነፃነት ለታገሉ የእውቅና እና የምስጋና ዝግጅት
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ተዘጋጅቷል። ዝግጅቱ የተደረገው በወልቃይት ጠገዴ ወፍ አርግፍ ከተማ ነው። በዝግጅቱ
የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ታጋዮች፣ የፀጥታ አባላትና የአካባቢው
ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በዝግጅቱም አሸባሪውን ሕወሃት በመታገልና የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራን ሕዝብ ነፃነት በመመለስ
ረገድ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትና ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል።
በእውቅናና ምስጋና ዝግጅቱ መልዕክት ያስተላለፉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው
አሻባሪው ሕዋሃት አማራ ጠል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ጠል ነበር ብለዋል። ሕወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ የፈፀመው በደል የከፋ
መሆኑንም አንስተዋል።
የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ታሪክ የሠራ ሕዝብ ነው ያሉት አቶ አሸተ ትህነግ የአማራን ማንነት
በማጠልሸት፣ በተጠና መልኩ በመጉዳት ሰላም በመንሳት ብዙ የክፋት ሥራ መሥራቱንም አንስተዋል።
የትህነግን ሀገር በታኝነት አስቀድመው የተረዱ ሀገር ወዳድ ታጋዮች እንደነበሩ ያነሱት አቶ አሸተ መራር ትግል አድርገው መልካም
ጊዜ አሳይተውናል ነው ያሉት። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ሕወሃት ሲመጣ ጀምሮ አምርሮ ታግሎታልም ብለዋል። የአማራ ሕዝብ
እውነተኛ ጥያቄ በውሸት ተደብቆ እንዳልቀረም ተናግረዋል።
ሕወሃት በለኮሰው እሳት ራሱን ለብልቦ ግብዓተ መሬቱ መፈፀሙንና ህወሃት በማለፉ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን
በስሙ የተነገደበት የትግራይ ሕዝብም ነፃ መውጣቱን ገልጸዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የዘር ማጥፋት ወንጄል ሲፈፀምበት ተው ያላሉ በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ገብተው ሕወሃትን
ከተደበቀበት ጉድጓድ ለማውጣት ሲጥሩ እያስተዋልን ዝም አንልም ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው።
“ኢትዮጵያ አሸባሪ ድርጅት ብላ የፈረጀችውን እየደገፉ መሆናቸውን ቃል በቃል ልንነግራቸው ይገባል፤ በሀገሪቱ ላይ ማንም አዛዥ
እንዲሆን አንፈቅድም፣ የፀጥታ ኀይሉን የማሠማራት መብት ያላቸው ኢትዮጵያውያን እንጅ የውጭ ኀይሎች ሊሆኑ አይችሉም”
ብለዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው ለመጣው ነፃነት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናም አቅርበዋል። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ለሚጠይቀው
ጥያቄ በአፋጣኝ መልስ አንዲሰጥም ጠይቀዋል።
ሰበዓዊነትና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው ያሉት አቶ አሸተ ለወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ሰበዓዊ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባልም ነው ያሉት።
በወልቃይት ጠገዴ የልማት እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m