የአማራ ልዩ ኃይል ሕዝብ ሊጠብቅ እንጂ ለወረራ አልመጣም፣ የልዩ ኃይሉ ተልዕኮ ሰላምን ማምጣትና ሕዝቡን መጠብቅ ነው” የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች

267

“የአማራ ልዩ ኃይል ሕዝብ ሊጠብቅ እንጂ ለወረራ አልመጣም፣ የልዩ ኃይሉ ተልዕኮ ሰላምን ማምጣትና ሕዝቡን መጠብቅ ነው”
የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ግፈኛ በንፁሃን ደም ሆዱን ይሞላል። በነፃ ሕዝብ ላይ ሴራ ይሸርባል። ስትበታተን
ደስ ይለዋል። አንድ ስትሆን ግን ይበሳጫሉ። ኃያልነታቸው በሰው ሀገር መፍረስና በንፁሃን ደም መፍሰስ ላይ የተመሠረቱ ሀገራት
ነፃ ሕዝብና ነፃ ሀገር አይወዱም። ፍላጎታቸው ከታላላቅ ሀገራት ጋር መወዳጄት ሳይሆን ትንንሽ መንደሮችን መፍጠር ነው።
ግፈኛ ፍትሕ ሲያገኝ ግፍ የተሠራበት ፍትሕ ያጣል። ኃያላን ነኝ ባዮች በኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን ለማስረዘም ጥረት እያደረጉ ነው።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ነዋሪዎች ደግሞ በነፃነታቸው ላይ ሴራ የሚሸርቡትን እያወገዙ ነው።
የአካባቢው ነዋሪ አወቀ መብራቱ ወልቃይት ጠገዴን የጦርነት ቀጣና ለማድረግ የታሰበው በአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና መከላከያ
ሠራዊት ትግል ነፃ ወጥቷል። ሕዝቡም ከተገዥነት ወደ ነፃነት ተመልሷል ነው ያሉት። ሕዝቡ ላገኘው ነፃነት የልዩ ኃይሉ ሚሊሻውና
መከላከያው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነውም ብለዋል። ሕዝቡ ደስተኛ ነው። አካባቢውንም በሚገባ እየጠበቀ ነው።
የአሜሪካ ጫና ተገቢነት የለውም። “የአማራ ልዩ ኃይል ሕዝብ ሊጠብቅ እንጂ ለወረራ አልመጣም፣ የልዩ ኃይሉ ተልዕኮ ሰላምን
ማምጣትና ሕዝቡን መጠብቅ ነው” ብለዋል። የአሜሪካን መግለጫ አንቀበለውም ከልዩ ኃይላችን ጋር ኾነን ስለ ሰላማችን
እንሠራለን ነው ያሉት። ሌላው የአካባቢው ነዋሪ ክብሮም ግርማይ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ሲበደል ኖሯል። አሁን ግን ሰላም
ሆኗል ነው ያሉት።
የአማራ ልዩ ኃይል በመርህ ተመስርቶ ሕዝብን ነፃ ያወጣ ኃይል ነው። የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ጀብዱ በተደጋጋሚ መነገርና
መወሳት አለበትም ነው ያሉት። የአማራ ልዩ ኃይል ተጋድሎ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ለዘላለም አይረሳም።
አሜሪካ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከመንካት አልፋ በነፃነታችን ላይ መጥታለችም ነው ያሉት። እኛ ነፃነታችን እያጣጣምን ያለን
ሕዝቦች ነንም ብለዋል። “የአማራ ልዩ ኃይል የእኛ ክፋይ ነው። የእኛ ልጆች፣ ወንድሞች፣ እህቶች ናቸው። ማንን ከማን ለመነጠል
ነው ልዩ ኃይሉ ይውጣ የሚሉት? ስለ አማራ ልዩ ኃይል ማውራት ያለብን አብረን የምንኖረው እኛ እንጂ በዓድ አካል አይደለም።
ነፃነታችንን ሰጠን ሰላማችንን ጠበቀልን እንጂ ምን አደረገን?” ነው ያሉት። የጠላቶቻችን ሐሳብ ከማውገዝ ባለፈ አንድነታችን
በማጠናከር እናሸንፋቸዋለንም ብለዋል።
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን የምታዝን ሳትሆን ትንንሽ መንደሮች እንድንሆን የምትሻ ሀገር ናትም ብለዋል። “በነፃነታችን ላይ
አትምጡብን። ዲፕሎማቶችና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሜሪካ ላይ ጫና ማሳደር አለባቸው። አሜሪካ ካሰበችልን ዝም
በማለት ትተባበርን። እኛ ሰላም ነን፤ እኛ ጋር የሚያገባት ነገር የለም” ብለውናል።
አሸባሪው ትህነግ ከወጣ በኋላ ሰላም ነን። ከልዩ ኃይሉና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት እየሠራን ነውም ብለዋል።
“ለወረራ የገባ ልዩ ኃይል የለም። በተቀናጄ መልኩ እየጠበቀን ነው። ስለ ሰላማችን እና ስለ ነፃነታችን ከእኛ በላይ የሚናገር
የለም” ነው ያሉት።
ስማቸው ካሳሁን ደግሞ ልዩ ኃይሉ ያመጣውን ሰላምና ነፃነት በቀላሉ መመልከት አይገባም ነው ያሉት። “የአሜሪካ መንግሥት
በትክክል ለሕዝብ ተቆርቋሪ ቢሆን መከላከያችንን የገደለን ቡድን ያወግዝ ነበር። የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ባይደርስ ኖሮ
ሟቾች ነበርን። የተቆረቆረ ሀገርና ሕዝብ የማይካድራውን ጉዳይ ይጠይቅ። የአማራ ልዩ ኃይል ሕዝብ ያተረፈ፣ ማንነትን የመለሰ
እንጂ እንደ ወያኔ ወንበዴ ህፃናትን የሚገድል አይደለም” ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ኢትዮጵያውያንን አለመረዳት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ለማንም ተገዝታ አታውቅም። ወደፊትም
አትገዛም። የሀገራቱ ጫና የበለጠ እንድንሠራ ያደርገናል እንጂ አያንበረክከንም ብለዋል። የአማራ ልዩ ኃይል ሕይወት ስለሰጠ
መወደስ እንጂ መወቀስ እንደሌለበትና ምንግዜም ከጎኑ እንደሚቆሙ አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአንዳንድ የውጪ ሀገር መንግሥታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ተደጋጋሚ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ተጠየቀ፡፡
Next articleኢትዮጵያዊያን “በውስጥ ጉዳዮቻችን ላይ የተዘረጉ የውጭ እጆች ይነሱ” ሲሉ ጠየቁ።