
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሀገራዊ ምርጫውን ለመታዘብ በአዲስ መልኩ ፈቃድ የሚጠይቁ ድርጅቶችን መቀበል
ማቆሙን አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ «የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች
ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011» እንዲሁም «የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ አሰጣጥ፣
አሠራር እና ሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 5/2012» በሚደነግገው መሠረት፣ ምርጫ ለመታዘብ ፍላጎት ያላቸውን የሀገር ውስጥ
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ይፋዊ ማስታወቂያ በማውጣትና በመመልመል በአንደኛ ዙር ለ36 ድርጅቶችን እውቅና መስጠቱን
አስታውሷል፡፡
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛ ጠቅላላ ምርጫን መታዘብ እንዲችሉ በመጀመሪያ ዙር አመልክተው ካልተመረጡ የሀገር ውስጥ
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከል ለቦርዱ ይግባኝ በማስገባት ይግባኛቸው በቦርዱ ታይቶ ውሣኔ ከተሰጠባቸው እና
በሁለተኛ ዙር እንደ አዲስ 6ኛ ጠቅላላ ምርጫን ለመታዘብ ማመልከቻ ካስገቡ ድርጅቶች መካከል ዘጠኝ የሀገር ውስጥ የሲቪል
ማኅበረሰብ ድርጅቶች 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መታዘብ እንዲችሉ ፍቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል፡፡
ማኅበራቱም
1. ማኅበረ ሕይወት ኢትዮጵያ – ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት
2. አልቢር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ኮኦፕሬሽን አሶሴሽን
3. ዲጂታል ሮግ ሶሳይቲ ኤክስፐርመንት ግሩፕ
4. ስፕሪድ የማኅበራዊ ችግሮች መፍቻ እና የልማት ድርጅት
5. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር
6. ሰኔ 16 የሰላምና የለዉጥ ተምሳሌት የሲቪክ ማኅበር
7. የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን
8. የአፍሪካ ልማትና ጥበቃ ተቋም
9. ሶሳይቲ ፎር ኢኮ ቱሪዝም ኤንድ ባዮ ዳይቨርሲቲ ኮንሰርቬሽን ናቸው፡፡
የተለያዩ ድርጅቶች አዲስ የምርጫ መታዘብ ፈቃድን የሚጠይቅ ማመልከቻ እያስገቡ እንደሚገኝ የጠቀሰው ቦርዱ ሀገራዊ
ምርጫው የሚከናወንበት ጊዜ እየተቃረበ በመምጣቱ፣ ካለው የተጣበበ ጊዜ አንጻር ለቦርዱም ሆነ ለማኅበራቱ ተገቢውን
የዝግጅት ሥራ ለመከወን አዳጋች በመሆኑ የመታዘብ ሥራ ጥያቄዎችን ቦርዱ መቀበል ማቆሙን ማስታወቁን በማኅበራዊ ትስስር
ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m