ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ፋሲል ከነማ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቴሌቶን ሊዘጋጅ ነው፡፡

346
ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ፋሲል ከነማ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቴሌቶን ሊዘጋጅ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 11/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ግንቦት 17/2013 ጀምሮ ˝ስፖርት ለኢትዮጵያ ሕብረት” በሚል መሪ ሀሳብ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ፋሲል ከነማ በአዲስ አበባ ከተማ የገቢ ማሳባሰቢያ ቴሌቶን እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጧል፡፡ በመግለጫው የተገኙት የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሞላ መልካሙ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያዊ ስሪት ያለውና ከሁሉም ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተገኙ ተጨዋቾች የነገሠ ክለብ ነው ብለዋል፡፡ ቡድኑም ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
”ፋሲል ከነማ ከክለብም በላይ ነው˝ ስንል ብዙ መሰዋዕትነት ተከፍሎ የተገኘ ክለብና በርካታ መሰናክሎችን አልፎ በዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ ክለቡ የራሱ ሃብት እንዲኖረው ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን ፤ ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ድርጅቶች፣ ተቋማትና ባለሃብቶች እንዲደግፉ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በበኩላቸው የጎንደር ከተማ አስተዳደር የሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ክለቡ ለድል እንዲበቃ አስተዋፆ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡
አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ስታልፍ የኢትዮጵያ አንድነት ታይቷል፤ አሁን እግር ኳሱ አድጎ በዓለም አቀፍና በአህጉር ደረጃ መሳተፍ ከተቻለ የኢትዮጵያን አንድነት ለማምጣት ከፍተኛ አስተዋጾኦ አለው ብለዋል፡፡
ሀገራዊ አንድነትና ሰላም የሚፈጥር ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመፍጠር ጠንካራ የእግር ኳስ ክለቦች መኖር ያስፈልጋል፤ ፋሲል ከነማንም በዘላቂነት ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት አሰልጣኝ ሰውነት።
በቴሌቶኑ አንድ ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡
ቴሌቶኑም ግንቦት 17፣ 20 እና 21 በአዲስ አባባ፣ በባሕር ዳር እንዲሁም በጎንደር እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleሀገራዊ ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና የምርጫ ሂደትን የጠበቀ እንዲኾን ወጣቶች የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡
Next articleበመጭው ክረምት ወቅት በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ከ30 ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞች እንደሚተከሉ የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡