“ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የጸጥታ ኀይሏን ያለማንም ይሁንታ እና ጣልቃ ገብነት የማሰማራት ሉዓላዊ መብት አላት” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

146

“ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የጸጥታ ኀይሏን ያለማንም ይሁንታ እና ጣልቃ ገብነት የማሰማራት ሉዓላዊ መብት አላት” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የቀረቡ ውንጀላዎችን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀገር በመሆኗ በውስጣዊ ጉዳዮቿ ላይ የየትኛውንም የውጭ ኀይል ጣልቃ ገብነት አትቀበልም ብሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ጉዳይ ለሚያሳስባቸው ተባባሪ አካላት በቂ ማብራሪያ እየሰጠ ቢሆንም የተወሰኑ ድርጅቶች ከውንጀላ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንዳልቻሉ ገልጿል።

የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሀገር በቀል እና እያደገ የሚሄድ ነው ያለው መግለጫው ዴሞክራሲን ለማሻሻል በውስጥ ጉዳያችን የየትኛውንም ሀገር ጣልቃ ገብነት አንፈቅድም ብሏል።

ኢትዮጵያ ባገጠሟት ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ የውጭ ኀይሎች ሁኔታዎችን ከማባባስ መቆጠብ አለባቸው ያለው የሚኒስቴሩ መግለጫ ለትብብር እና አብሮ ለመሥራት ግን በራችን ክፍት ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ በሀገራዊ የውስጥ ጉዳይ ሉዓላዊነቷን በጣሰ መንገድ እንደማትደራደር በድጋሚ ግልፅ አቋሟን ለማንፀባረቅ ተገደናል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው።

የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ውንጀላዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክሶችን እና ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር የቀረቡ ቅድመ ሁኔታዎችን መሰረተ ቢስ ውንጀላዎች ብሏቸዋል። ቀጣዩን ሀገራዊ ምርጫ ግልጽ እና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

የአማራ ልዩ ኋይልን በሚመለከት ለቀረበው ውንጀላም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መልስ ሰጥቶበታል። “ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የጸጥታ ኀይሏን ያለማንም ይሁንታ እና ጣልቃ ገብነት የማሰማራት ሉዓላዊ መብት አላት” ብሏል።

በታዘብ አራጋው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ሰላም፤ እርጋታ እና የዜጎች ደኅንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው”በአሜሪካ የኢትዮጵያ የሕዝብ ዲፕሎማሲያዊ አማካሪ ምክር ቤት
Next article“ከክልሉ ውጭ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ትርጉም ባለው መንገድ አልተሠራም” ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም