በአንድ ዓመት ውስጥ ለ50 ሺህ ከስደት ተመላሽ ሴቶች የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር ፕሮጀክት ተጀመረ።

106
በአንድ ዓመት ውስጥ ለ50 ሺህ ከስደት ተመላሽ ሴቶች የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር ፕሮጀክት ተጀመረ።
ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከጃምቦ የጽዳት አገልግሎት ጋር ለከስደት ተመላሽ ሴቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ለማስጀመር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ፕሮጀክቱ ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች የሚመለሱ ሴቶች በጽዳት፣ በምግብ ሥራና የቤት ለቤት አገልግሎቶች በመሠማራት ገቢ የሚያገኙበትን ሥርዓት ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር የሚተገበር ነው ተብሏል።
ሴቶች በሌሎች ሀገራት በሚሠሩባቸው የሥራ ዘርፎች ተግባራዊ ልምድ ያካበቱ በመሆኔቸው በቀላሉ ወደሥራ ለመግባት የሚችሉ መሆናቸውን የጃምቦ የጽዳት አገልግሎት ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል።
የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ንጉሡ ጥላሁን ከስደት ተመላሽ ፕሮጀክቱ ለግሉ ዘርፍ አካላት መልካም ተሞክሮ እንደሆነ ገልጸዋል። “ፕሮጀክቱ በመጪው አንድ ዓመት 50 ሺህ ከስደት ተመላሽ ሴቶችን በአንድ ዓመት ወደሥራ ለማስገባት መዘጋጀቱ ኮሚሽኑ ትኩረት ከሰጠው የሥራ ገበያ አካታችነት አንጻር ሲመዘን ጥሩ ጅማሮ መሆኑን ያመላክታል” ብለዋል።
በፕሮጀክቱ የሚካተቱ ሴቶች በቅድሚያ የ16 ቀናት የሥነልቦና ዝግጁነት፣ የብቁ ባለሙያነት፣ ጠቅላላ የጽዳት ሥራና የምግብ ዝግጀት ማጎልበቻ አጭር ስልጠናዎችን የሚወስዱ ይሆናል ተብሏል። ባለሙያዎቹን ከአሠሪዎች ጋር የሚያገናኝ የኦንላይን መተግበሪያ መዘጋጀቱንም ከሥራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነትም የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ተጠቃሚዎችን የመመልመል እና ሌሎች መንግሥታዊ ድጋፎችን በበቂ ሁኔታ በመፈፀም የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበሰሜን ሽዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በተፈጠሩ ግጭቶች የተፈናቀሉ ወገኖችን እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም መልሶ ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
Next article“ሰላም፤ እርጋታ እና የዜጎች ደኅንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው”በአሜሪካ የኢትዮጵያ የሕዝብ ዲፕሎማሲያዊ አማካሪ ምክር ቤት