
በሰሜን ሽዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በተፈጠሩ ግጭቶች የተፈናቀሉ ወገኖችን እስከ ሰኔ 30/2013ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ ለማቋቋም ከ945 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት
ለማስበሰብ እየተሠራ መሆኑንም የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ
ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በሰሜን ሽዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢዎች በተፈጠረ የጸጥታ ችግር የሰው ሕይዎት አልፏል፣ ከተሞች
ፈርሰዋል እንዲሁም በርካታ ሕዝብ ከመኖሪያ ቀየው ተፈናቅሏል፡፡ በጸጥታ ችግሩ ምክንያት ከ311 ሺህ ሕዝብ በላይ ከመኖሪያ
ቀየው ተፈናቅሎ በጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኝ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ
አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነሩ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ለብዙኃን መገናኛ ተቋማት በሰጡት መግለጫ የተፈናቀሉ ወገኖችን እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም
ድረስ መልሶ ለማቋቋም እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡ ተፈናቃዮቹን መልሶ ለማቋቋም ከ945 ሚሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል ያሉት
ኮሚሽነር ዘላለም በክልሉ እና ከክልሉ ውጭ ሃብት ለማሰባሰብ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር የሚመራ ቡድን በክልሉ ውስጥ እና ከክልሉ ውጭ ሃብት ለማሰባሰብ ደግሞ በአማራ ልማት
ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ የሚመራ ቡድን በአዲስ አበባ ተቋቁሞ ሃብት እያሰባሰበ መሆኑን ኮሚሽነር ዘላለም
በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡
ከሃብት ማሰባሰቡ ጎን ለጎን የክረምት ወቅት ሳይገባ ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ከ11 ተቋማት የተውጣጣ እና የመልሶ
ማቋቋም ሥራዎችን የሚሠራ ቡድን ተቋቁሞ ወደ አካባቢዎቹ ተሠማርቷል ተብሏል፡፡
መጭው ወቅት ክረምት በመሆኑ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች እንዳያሳልፉ እና አርሶአደሮች ወደ እርሻ ሥራዎቻቸው
ካልተመለሱ በሚቀጥለው ዓመትም ለችግር ስለሚጋለጡ በተቀመጠው ጊዜ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ
ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡
የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ እና ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው በመመለስ የክረምቱ የእርሻ ወቅት እንዲጠቀሙ ማድረግ
ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ተብሏል፡፡
ለመልሶ ማቋቋም የሚያስፈልገውን ሃብት በማሰባሰቡ ተግባር ውስጥ ሕዝብ እና ተቋማት ተሳታፊ እንዲሆኑም ከሚሽነር ዘላለም
ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
