
ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 01/2011 ዓ.ም(አብመድ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 2ኛ ሳምንት የውጤት መግለጫዎች
አቃቂ ቃሊቲ ወሎ ኮምቦልቻን 1ለ0፣ ደሴ ከተማ አውስኮድን 2ለ0 አሸንፈዋል፡፡
አክሱም ከሰበታ ከተማ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ፌደራል ፖሊስ ከኢትዮ-አሌክትሪክ ባዶ ለባዶ፣ ወልድያ ገላን ከተማን 3ለ0 ለዜሮ ሲረታ ግቦቹን ተስፋዬ ነጋሽ እና ኢድሪስ ሰዒድ በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ውጤቶች፡-
• ኢትዮጵያ ቡና 1-1 ወላይታ ዲቻ ሲለያዩ ግቦቹን ካሉሻ አልሀሰን እና ኢዮብ አለማየሁ አስቆጥረዋል፡፡
• ሀዋሳ ከተማ አዳማ ከተማን 2ለ0 ሲያሸንፍ ታፈሰ ሰለሞንና እስራኤል እሸቱ ደግሞ የግቦቹን በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡
• ስሑል ሽረና የአምናው ሻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር ያለግብ ጨዋታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡
• ድሬድዋ ከተማ ደደቢትን በሜዳው ጋብዞ 2ለ0 አሸንፏል፡፡ ግቦቹን ኢታሙና ኬሙ ይኔ እና ፍቃዱ ደነቀ አስቆጥረዋል፡፡ ምንጭ፡- ሶከር ኢትዮጵያ
የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ

• ትናንት በተካሄደ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ግጥሚያ ኒውካስትል በወልቨር ሃምፕተን ወንደረርስ 2ለ0 ተሸንፏል፡፡ ዲያጎ ጆታና ማት ዶሆርቲ ለወልቭስ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡ ዲአንድሬ የድሊንን በቀይ ያጣው ኒውካስትል ብቸኛዋን ግብ በአዮዝ ፔሬዝ አማካኝነት አግኝቷል፡፡

የስፔን ላሊጋ
• በስፔን ላሊጋ ደግሞ በዚህ ዓመት ከውጤታማነት የራቀው ሪያል ማድሪድ በጋሪዝ ቤል ብቸኛ ግብ ሁሴካን አሸንፏል፡፡ የሌቫንቴ እና ኢባር ጨዋታ ደግሞ ከግማሽ ደርዘን በላይ ግብ ተስተናግዶበት 4ለ4 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ ሌቫንቴ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ሪያል ቤትስ ራዮ ቫልካኖን ሁለት ለባዶ ረትቷል፡፡ ሪያል ቫላዶሊድ ደግሞ ሪያል ሶዴዳን 2ለ1 አሸንፏል፡፡
ስካይ ስፖርት
በኪሩቤል ተሾመ