
ባሕር ዳር: ግንቦት 05/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፓርቲው ደጋፊዎች የምርጫ ካርድ ከመወሰድ ጀምረው በቅድመ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም በምርጫና በድሕረ ምርጫ ወቅት በንቃት በመሳተፍ ለአካባቢያቸው ሰላም የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናረዋል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ በቅርቡ ለሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ የፓርቲውን መርሃ ግብር ከማስተዋወቅ ጀምሮ የክልል ምክርቤት እጩ ተወዳዳሪዎችን ለኀብረተሰቡ እያስተዋወቀ ነው ብለዋል፡፡
ከምርጫ ሥራ ጎን ለጎን ለአካባቢው ሰላም ሕዝቡ ዘብ እንዲቆሙም ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ሰለሞን አወቀ- ከስማዳ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m